የሥግድ በዓል - የኢትዮጵያ አይሁዲ ቅርስ ማዕከል

የሥግድ በዓል

የስግድ በዓል ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የተገባበትን ያስታዉሳል ፡፡ እያናዳናዱ ቤተ እስራኤል የሆነ ሁሉ ልቡን ወደ ፈጣሪ እዙሮ እጸለየ ስለ እየሩሳሌም ጽኑ የሆነ ምኞቱንና ጉጉቱን የሚገልጽበት ቀን ነው ፡፡
የሥግድ በዓል ለኢትዮጵያ ይሁዲወች ልዩ ቦታ አለው ፤ በዚህ ቀን ቤተ እስራኤሎች የራሳቸውን ሃይማኖታዊ፤ መንፈሳዊና ማህበረ ሰባዊ አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት ቀን ነው፡፡
ሥግድ የሚለው ስም " መስገድ " ከሚል ቃል የተወሰደ ሲሆን ፤ ከሴም ቋንቋ ቃል የተወሰደ ፤ ጎንበስ ብሎ መስገድ ማለት ነው ፡፡ ስለሆነም በሥግድ በዓል ቀን ይህ ቃል ለዩ የሆነ ይዘት አለው፤" ለእግዚአብሔር ጎንበስ" ማለት " ምሕለላ" ተብሎም ይጠራል፤ (ይቅር በለኝ ብሎ ፈጣሪን መማጸን) ፡፡ "
የባዓሉ መነሻ ይሁዲወች ከባቢሎን ሥደት ወደ ጺዮን ሲመለሱ በመጽሃፈ ዕዝራና ነሀሚያ እንደሚተረከው ሕዝቡ ወደ ህይማኖቱ ተመልሶ የእግዚብሔር አገልጋይ እንዲሆን ጉባኤ ተደርጎ የተመከረበት ቀን ነው፡፡" ዕዝራ ከሕዝቡ ከፍ ብሎ በተሠራው መድረክ ላይ በቆመ ጊዜ ሁሉም ትኩር ብለው ይመለከቱት ነበር ፤እርሱም የሕጉን መጽሐፍ በከፈተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ከተቀመጠበት ተነሣ ፡፡ ዕዝራም " ታላቅ አምላክ የሆነ እግዚአብሔር ይመስገን " አለ ፡፡ ሕዝቡም ሁሉ እጃቸውን ወደ ላይ በማንሣት " አሜን አሜን " ሲሉ መለሱ ወደ ምድርም ለጥ ብለው ፊታቸውን መሬት በማስነካት ለእግዚአብሔር ሰገዱ ፡፡ ከዚህ በኋላ ተነስተው ባሉበት ስፍራ ቆሙ ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው የተዘረዘረ ሌዋውያንም የሕጉን መጽሐፍ ትርጉም ለሕዝቡ ገለጡላቸው ፡፡ እነርሱም ፤ ኢያሱ ፤ ባኒ ሼሬብያ ፤ ቀሊጣ ፤ ዐዛሪያ ፤ ዮዛባድ ፤ ሐናንና ፐልያ ነበሩ ፡፡

ያለፉት አጋጣሚዎች

November 23
የስግድ በዓል በእየሩሳሌም 2022

የስግድ በዓል በእየሩሳሌም

ቦታውም በኢየሩሳሌም አርሞን ሃናጺብ አጠገብ በሚገኘው ታየሌት ሽሩበር በተባለው መናፈሻ ቦታ ነው
23.11.2022 08:00 - 14:00
በእየሩሳሌም ከተማ በሚካሄደው የስግድ በዓል ማዕከላዊ የጸሎት ስነ ስርዓት አከባበር እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል በዓሉ የሚከበረው ረቡዕ ህዳር(ኖቬምበር) 23 ቀን 2022 ዓ/ም ካፍ-ቴት በሄሽቫን- ታፍ-ሺን-ፔ-ጊሜል ሲሆን ቦታውም በኢየሩሳሌም አርሞን ሃናጺብ አጠገብ በሚገኘው ታየሌት ሽሩበር በተባለው መናፈሻ ቦታ ነው የጸሎቱ ስነ ሥራዓት መድረክ በ 8፡00 ሰዓት ይጀምራል የበዓሉ መንግሥታዊው አከባበር በ12:30 ሰዓት ይካሄዳል በዚሁ ቀን ከእየሩሳሌም አውቶቡስ ጣቢያ(ታሃና መርካዚት) ዝግጅቱ ወደሚከናወንበት ቦታ የሚወስዱ ልዩ የህዝብ ማጓጓዣዎች ተዘጋጅተዋል:: በተጨማሪም ከመላው ሀገሪቱ ወደ እየሩሳሌም የሚወስዱ አውቶብሶችም ተዘጋጅተዋል:: የአውቶቡሶችን መነሻ ጊዜ እና ቦታ ለማወቅ በአካባቢ ያሉትን መስተዳድሮች በመጠየቅ ወይም የማስታወቂያ ክፍል ቢሮ ድረ ገጽ በማየት ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል:: https://www.gov.il/he/departments/hq-for-state-ceremonies-and-events
November 13
የስግድ ጸሎት በእየሩሳሌም

የስግድ ጸሎት በእየሩሳሌም

በእየሩሳሌም አርሞን ሀናጺቭ መናፈሻ ተራራ
13.11.2023 09:30 - 13:00
አገራችን ባለችበት "የብረት ሰይፎች" ጦርነት ምክንያት እና በደጀን እዝ (ፒኩድ ሀዖሬፍ) መመርያ መሰረት፣ የስግድ ጸሎት በካህናት ተሳትፎ ብቻ በእየሩሳሌም አርሞን ሀናጺቭ መናፈሻ ተራራ ይካሄዳል፡፡   ማህበረሰቡ በየአለበት ቦታ ጸሎቱን እንዲከታተል፣ ከእየሩሳሌም በቀጥታ ስርጭት በኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል እና ቅርስ ማእከል ድረ-ገጽ፣ ዩቲዩብ እና ፌስቡክ   ከ 9፡30 እስከ 13፡00 ሰዓት መከታተል ይችላል።   ከጸሎቱ በኋላ የክብር እንግዶች ንግግር አይደረግም፡፡ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ፣ በኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል እና ቅርስ ማእከል፣ በካህናት-የሐይማኖት አመራር እና የክብረ በዓላት እና መንግስታዊ ዝግጅቶችን አቀናባሪ ክፍል ተዘጋጀ