መዳረሻቸው ስለጠፋ ስወች – የኢትዮጵያ አይሁዲ ቅርስ ማዕከል

መዳረሻቸው ስለጠፋ ስወች

እየሩሳሌም ፤ የሩሻላይም ለመድረስ የብዙ ሽህ ዓመት ሕልማችሁን እዉን ለማደርግ ከቤታችሁ በወጣችሁበት ቀን፤ አብዛኞቻችሁ የተደራጁ ስዎችን በሌሊትና በቀን በበርሃና በገደል ፤ በኢትዮጵያ ጫካወችና የሱዳን በረሃን በማቋረጥ ፤ በርሃብና በጥማት ሰዎችን በመምራት ፤
ለራሳችሁ ሳታስቡ ዋነኛ ዓላማችሁ ይሁዲወች ሕልማቸውን እውን እንዲድደርጉ ለመተባበር ነው የነበረ ፡፡በጉዞ ላይ ደክመው የነበሩት ሁሉ አንዲበረቱ ትልቅ ምሳሌወች ሆናችኋል፤
በዙ ዓመታት አለፉ፤ እናንተ ግን ስታልሟት ከቆያችሁት እየሩሳሌም አልደረሳችሁም፤ ከኋላ ወላጆች ወንድሞችና እህቶች ጥላችሁ ነው የሄዳችሁት፤
እኛ ከተስፋይቱ አገር ገብተናል እናንተም ጉዟችሁን በተሎ ጨርሳችሁ ሕልማችሁን እዉን እንድታደርጉ በየቀኑ ጸሎት በማድረግ እንጠባበቃለን፤
” ቀና ብላችሁ ወደ ሰማይ ተመልከቱ ፤ እርሱ እንደ ሠራዊት ይመራቸዋል ምን ያህል እንደሆኑም ቁጥራቸውን ያዉቃል ” ( ኢሳያስ ምዕራፍ 40 ቁጥር 26 )

የጠፉትን ሰወች ስም በዝርዝር ግለጽ