በእስራኤል ሃገር ክሊታ (አኗኗር) - የኢትዮጵያ አይሁዲ ቅርስ ማዕከል

በእስራኤል ሃገር ክሊታ (አኗኗር)

በ 80ዎች ዓ/ም በሱዳን በ90ዎች ዓ/ም በቀጥታ እሥራኤል የገቡት የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ( ቤተ እሥራኢሎች ) በተለይ "ሚብጻ አኺም " ተብሎ እየተጠራ በመላው 80ዎች ዓ/ም በተካሄድው ጉዞ እና በ1991 ዓ/ም " ሚብጻ ሽሎሞ " በተባለው ጉዞ ነው አብዛኛዎች የኢትዮጵያ ይሁዲዎች እሥራኢል የገቡ ፡፡
የኢትዮጵያ ይሁዲዎች አልያ አስከ ዛሬ ደረስ እንደቀጠለ ሲሆን ለመምጣት በመጠባበቅ ላይ የሚገኙትም ብዙዎች ናቸው ፡፡ አዲስ ገቢዎች እሥራኤል ሲደርሱ በመጀመሪያ ሚርካዝ ክሊታ ( ማስተናገጃ ቦታ) በልዩ ሁኔታ ከተዘጋጀ የካራቫን ቤቶችና ሌላም የእንግዳ መቀበያ ቦታዎች ገብተው ፤ በሶኽኑት ሃይሁዲት መሥሪያ ቤት ሃላፊነት እንክብካቤ ይደረግላቸዋል ፡፡
እነዚህን ቦታዎች በሃላፊነት የሚያስተዳድሩት ሰዎች ፤ አዲስ የኑሮ ዘዴ ካላት እሥራኤል አገር የመጡት አዲስ ገቢዎች በጤና ፤ በትምህርት ፤ በሥራና በሌላም አስፈላጊ በሆኑት ጉዳዮች ሁሉ ለአዲስ ገቢዎች መሠረታዊ ሥልጠናዎችን ይቀበላሉ ፡፡
ከሚርካዝ ክሊታ የመቆየት ጊዜያችውን አጠናቀው ወደ ቋሚ መኖሪያ ቤታቸው ሲያልፉ እንዳይቸገሩ ለማድረግ ልዩ ዕቅዶች ይዘጋጃሉ ፡፡ ለምሳሌ ፤ ሞኬድ ክሊታ ፤ በመከላክያ ሠራዊት ማገልገል ያለባችው ወጣቶች ቀስ ብለው መለማመድ እንዲችሉ ልዩ የሆነ ዕቅድ ማዘጋጀት ፤ ሥራ ለማኘት የሚያስችሉ ልዩ የሆኑ የሙያ ሥልጠናዎችን መስጠት፤
ስለሆነም የዚህ ዓይነት መላካም አመለካከት ያልተጠበቁ ችግሮችን ሊፈጥር ችሏል ፤ ይህውም ፤ አዲስ ገቢዎችና ልጆቻቸውም በነባሩ የእሥራኤል ዜጎች በኩል እንደ ለዩ ፤ ለብቻ የተገለሉ መስለው ስለታዩ የአድልዎ እና የዘረኛነት አመለካከቶች በግላዊና በተደራጀ ሁኔታ ሊያስከትሉ ችለዋል ፡፡

New immigrants from Ethiopia in their immigration centre at Hulda. Photo: Peer Vered, IPPA
Photo: Peer Vered IPPA
KINDERGARTEN TEACHER TAKING HER ETHIOPIAN CHILDREN FOR A WALK IN THE ABSORPTION CENTER AT KIRYAT GAT. Photo: Nati Harnik GPO
Photo: Nati Harnik, GPO
AN ETHIOPIAN IMMIGRANT LISTENING TO A RADIO ON A BENCH AT
Photo: Amos Ben Gershom, GPO
P.M. YITZHAK RABIN SPEAKING WITH NEW ETHIOPIAN IMMIGRANT RESIDENTS OF THE NAHAL BEKA CARAVAN NEIGHBORHOOD. Photo: Avi Ohayon, GPO
Photo: Avi Ohayon, GPO
NEW IMMIGRANTS FROM ETHIOPIA STUDYING HEBREW IN A SAFED ABSORPTION CENTER ULPAN
Photo: Elpert Nathan, GPO
NEW ETHIOPIAN IMMIGRANTS LEARNING HEBREW IN A CLASS AT THE ASHKELON ABSORPTION CENTER. Photo: Nati Harnik, GPO
Photo: Nati Harnik, GPO
SINGING AND DANCING AT KFAR TABOR MOBILE HOMESITE,WITH CHILDREN FROM NEARBY MOSHAVIM, OPERATION SOLOMON, ETHIOPIAN IMMIGRANTS. Photo: Doron Horowitz, GPO
Photo: Doron Horowitz, GPO
ETHIOPIAN IMMIGRANTS DEMONSTRATING IN FRONT OF THE CHIEF RABBINITE IN JERUSALEM, AGAINST THE RABBINITES REFUSAL TO RECOGNIZE THEM AS JEWS. Photo: Nati Harnik, GPO
Photo By: Nati Harnik, GPO
ETHIOPIAN IMMIGRANTS DEMONSTRATING OUTSIDE THE KNESSET AGAINST PATRONIZING OFFICIAL ATTITUDES TO THEIR ABSORPTION BY THE CHIEF RABINATE, THE JEWISH AGENCY. Photo: Nati Harnik, GPO
Photo: Nati Harnik, GPO
IMMIGRANT BOYS FROM ETHIOPIA AT GADNA TRAINING IN A MILITARY BASE IN THE NORTH. Photo: Nati Harnik, GPO
Photo: Nati Harnik, GPO
ONE OF THE GADNA RECRUITS IN HIS CLASSROOM DURING A LECTURE ON ZIONISM. Photo: Nati Harnik, GPO
Photo: Nati Harnik, GPO
NEWLY ENLISTED ETHIOPIAN IMIGRANT BOYS ON PARADE AT GADNA (YOUTH BATTALION) CAMP IN THE NORTH. Photo: Nati Harnik, GPO
Photo: Nati Harnik, GPO
A TOAST FOR OPERATION SOLOMON Photo by Vered Peer,IPPA
Photo by: Vered Peer, IPPA

መኖሪያ ቤት

ቀደም ሲል እንደተገለጸው በ 80 ዎችና በ 90 ዎች ዓ/ም እስራኤል የመጡት የኢትዮጵያ ይሁዲወች ከሌላ ሃገራት እንደመጡት ይሁዲወች በቀጥታ ቋሚ መኖሪያ ቤት አይደለም የተሰጣቸው፡፡ ከአዲስ ገቢዎች ማስተናገጃና ከሚርካዝ ክሊታ ነው ለብዙ ጊዜ የቆዩት፡፡ ይህን የመሰለ ውሳኔ የተላለፈበት ምክኒያት ፤ የአዲስ ገቢዎች ዕውቀት ደርጃ ዝቅተኛ ስለሆነና ይዘውት የመጡት ሃብት በእጅጉ አነስተኛ ሰለሆነ ፤ እንዲሁም ሌላ ተጨማሪ ምክኒያቶችንም በመስጠት ነበር፡፡
በተላለፈው ደንብ መሰረት ከኢትዮጵያ የመጡት አዲስ ገቢወች ለአምስት ዓመታት ተሚርካዝ ክሊታ ይቆዩ የሚል ነበር ፡፡ የመጀመሪው ሂደት ለአንድ ዓመት ከጊዜያዊ ሚርካዝ ክሊጣ ቆይተው ወደ ቋሚ መኖሪያ ቤት እንዲያልፉ ሆነ ፡፡
በ 80ዎች ዓ/ ም አብዛንጋዎች አዲስ ገቢወች በመንግስት ከተዘጋጁት የተወሰኑ ቦታወች ፤ በተለይ ከማህል አገር ራቅ ካሉት ከተሞች ቤት ተሰጣቸው ፡፡ በ 90 ናዎች ዓ/ ም ፤ ከሚብጻ ሞሼ በኋላ ግን ቀደም የነበረው ደንብና መመሪያ ተቀየረ ፤ መክኒያት የሆነውም፤ አዲስ ገቢዎችን ከማሃል አገር ርቀው ከሚገኙ ከተሞች ሂደው እንዲኖሩ መደረጉ ከባድ የሆነ የማህራዊ ለዩነት እየፈጠ መሆኑ ሰለታየ ነው ፡፡ ከ 1991 ዓ/ ም በኋላ እሥራኤል የገቡት ፤ ከመንግስት የቤት መግዥ ገንዘብ ( ማሽካንታ ) ተሰጥቷቸው ጠንካራ ህብረተ ሰብ ከሚኖሩባቸው ከተሞች ሳይሆን ከተወሰኑ ከተሞች ብቻ ቤት እንዲገዙ ተወሰነ ፡፡ ስለሆነም የዚህ ዓይነት መመሪያና ውሳኔ፤ ከኢትዮጵያ የመጡት አዲስ ገቢዎች ቤት እየገዙ የሚገቡት ችግረኛ ነባር ህብረተ ሰብ ከሚኖሩባቸው ከተሞችና ሠፈሮች ሆነ ፡፡

ሥራን ባስመለከተ

አንደኛ ፤ በሚብጻ ሞሸ እስራኤል የገቡት ቤተ እስራኤሎች የሥራ ቦታ እንዲያገኙ ለማድረግ ልዩ የሆነ መርሃ ግበር ማዘጋጀት አስፈላጊ ለመሆኑ በሃላፊነት የሚሰሩት ሁሉም አመኑበት፡፡ከኢትዮጵያ የመጡት ይሁዲወች ያላቸው የስራ ልምድ ከእስራኤሉ ጋር የሚመቻች ሁኖ ስላልተገኘ ፤ ይህን የመሰለ ዕቅድ ለማውጣት ፤ የክሊታ ምኒስትር ጽህፈት ቤት ፤ የሥራና አሰሪ ጉዳይ ፤ የትምህርት ምኒስትርና ፤ እንዲሁም ጆይንትና የሶህኑት ሃይሁዲት ሰውችም የተሳተፉበት አካል ተቋቋመ ፡፡ በመጀመሪያ ለኢትዮጵያ ይሁዲወች ብቻ የሚሆኑ የሙያ ሥልጠና ለመስጠት ፡፡፤ ስልጠናውም የአዲስ ገቢወች የትምህርት ደረጃና በጾታ የተመደበ ነበር፡፡ ወንዶች በአብዛኛው በፋብሪካ ቦታወችና በግምባታ ሥራ፤ እሴቶች ለአዙዉንት እንክብካቤ አሰጣጥ በልብስ ስፌትና አንጠረኛነት፤ 12 /ኛ ክፍልና ከዚያም በላይ ያጠናቀቁትን ፤ በእርዳት የጥርስ ህክምና ፤ ከህብረተ ሰብ ጋር የመስራትና በሂሳብ ሠረተኛነት፡፡
ሁለተኛ፤ አዲስ ከሆነባቸው የስራ ባህሪ ጋር መለማመድ እንዲችሉ ለማደርግ ፤ ልዩ የሆነ ትምህርታዊ ገለጻ መስጠትና መቆጣጠር ፡፡ ይህን የሚያደርጉት ሰወች የሙያ ሥልጠና ከተስጣቸው አዲስ ገቢወች ጋር አብረው ሲከታተሉ የቆዩት ሲሆኑ ለስራ የሰለጠኑት ሁሉ የስራ ቦታ ማግኘታቸውንና ከሚሰሩበት ቦታ መብታቸው የተከበረ መሆኑን መከታተልና ቁጥጥር ማድረግ ነው ፡፡
ከ 90 ናዎች ዓመታት ጀምሮ ለኢትዮጵያ አድስ ገቢወች ተጨማሪ አዳዲስ ዕቅዶች ተዘጋጅተዋል፤ ለምሳሌ፤ ኤሸት ሀይል የሚባለው ለሴቶች አዳዲስ የስራ ዕድል የሚፈጥርና ጥቃቅን ቢዝነሶችን መክፈት የሚያስችሉ አጋጣሚወችን በመፍጠር፡፡

ስለ ትምህርት

በ 80ኒዎች ዓ/ም እስራኤል የገቡት ቤተ እስራኤሎች ከመንግሥታዊ የሃይማኖት ት/ቤቶች እንዲማሩ የተወሰበት ምክኒያት ፡፡ እነሱ ሃይማኖታዊ ስለሆኑ ከአዲሱ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ይዘት ጋር መለማመድ እንዲችሉ ለማድረግ ነው የሚል ነበር፤ የዚህ ዓይነት ዉሳኔ ከወላጆች ጋር ምክክሮች ሳይደረጉና ወላጆች
ልጆቻቸውን ከፈለጉት ቦታ እንዲማሩ የመምረጥ መብታቸውን ባለማክበርና ከህብረተ ሰቡ ጋርም ሳይመከርበት የመንግሥትን ቋሚ መመሪያም በመጣስ ነበር የተወሰነ ፡፡
ሌላው ተጨማሪ ዉሳኔም፤ የአዲስ ገቢወች ለጆች ” አሊያት ሃኖአር” ከሚባለው ሃይማኖታዊ አዳሪ ትምህርት ቤት ገብተው ይማሩ የሚል ነበር ፡፡ የዚህ ዓይነት መረሃ ግብር የታሰበውን ውጤት አላስገኘም፤ አንደኛ ፤ የኢትዮጵያ ይሁዲ ወጣቶች የተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶች ብቻ
እንዲማሩ መወሰኑ ራሱ ስህተት መስሎ ተገኘ በተለይ በ 1992 ዓ/ም የመጡት ወጣቶች ለሙያ ትምህርት እንጅ ለቀጣይ ትምህርት የሚረዳ የትምህርት ዕድል አልነበረም የተሰጣቸው ፡፡
ሁለተኛ ፤ ልጆች ከወላጆቻቸው ተለይተው ሩቅ ቦታ ሰለተላኩ ወላጆች ስለ ልጆቻቸው ትምህርት ጉዳይ መወስንና መከታተል አልቻሉም፤፡፡ በ 80 ዎች ዓ/ ም የመጡትን አዳሪ ትምህርት ቤት ለመላክ መወሰኑ በቂ ምክኒያት ነበረው ፡፡ ምክኒያቱም በዚያን ጊዜ እሥራኤል የመጡት ወጣቶች ከወላጆቻቸው ጋር አልነበረም ፡፡( ከወላጆች ጋር የመጡ ቢኖሩም እነሱም በጅምላ ነው አዳሪ ት/ ም ቤት የተለኩት ) በሚብጻ ሽሎሞ ለመጡት ግን አዳሪ ትምህርት ቤት መላኩ ተስማሚ አልነበረም ፡፡ አብዛኞች ከቤተ ሰቦቻቸው ጋር ስለመጡ፡፡ ከ 90 ምዕተ ዓመት መሃከል ላይ ጀምሮ ወደ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚላኩት ወጣቶች ቁጥር እየቀነሰ ሄዷል ፡፡

ብሔራዊ መ/ ሠራዊት

በ 80 ዎች ዓ/ም መጀመሪያ አካካባቢ ከኢትዮጵያ እስራኤል የመጡትን ወጣቶች ከብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት ተቀጥረው ማገልገል እንዲችሉ ለማድረግ፤ የመከላከያ ሠርዊት ፤ ሃሶክኑት ሃይሁዲትና የክሊታ ምኒስቴር ጽህፈት ቤቶች በመተባበር ለዩ መርሃ ግብር አዝጋጁ ፡፡ ዕቅዶችም ፟፤ ለመከልከያ ሠራዊት ምልመላ በፊት ለወጣቶች ቅድመ ዝግጅትና ቅድመ ሥልጠና መስጠት ፤ ተቀጥረው በሚያገለግሉበት ጊዜ አስፈላጊ እርዳታወችን መስጠትና አገልግሎታቸውን አጠናቀዉ የመሰናበቻ ጊዜያቸው ሲቃርብ ምን ማደርግ እንዳለባቸው  አቅጣጫ መሪ የሆኑ ምክሮችን መስጠት ፡፡ ወጣቶች ወታደራዊ መለዮ ተቀብልው በይፋ ከሠራዊቱ ከመግባታቸው በፊት ማጌን ጺዮን የሚል ስም በተሰጠው ቅድመ ዝግጅት ለሦስት ወራት ሥልጠና ይሰጣቸዋል ፡፡ የዚህ ልዩ ይዘት አይነተኛ ዓላማ፤ ወጣቶች የዉትድርና ባህሪ ምን እንደሆነ እንዴት አድርገው መለማመድ እንደሚችሉና እንዲሁም የዕብራይስጥ ቋንቋ ችሎታቸው ተሻሽሎ ስለ እስራኤል ሃገር ታሪክ ለማስተማር ሲባል ነው ፡፡ በመጀመሪያ ከኢትዮጵያ የመጡት ወጣቶች ሁሉም ወደዚህ ቦታ ነበር በጅምላ የተላኩት ( የመቃወም መብት ቢኖራችወም ) በ 90 ናዎች ምዕተ ዓመት ለዉጦች እንዲደረጉ ተወሰነ ፡፡ ይህዉም፤ ለመከላከያ ሠራዊት የሚመለመሉትን እንደየ ችሎታቸው ለሦስት ደረጃ በመክፈል፤ በመጀመሪው ዕቅድ መሰረት በችሎታቸው ያረጋገጡ ፤ ለሦስት ወራት ብቻ ልምምድ ያጠናቀቁ ፤ እና እንደማንኛዉም ወጣት ከመከላከያ ሠራዊት የሚቀጠሩ፤፡፡
ከብሄርዊ መከላከያ ሠራዊት በሚያገለግሉበት ጊዜ  በሃላፊነት የሚከታተል ልዩ ወታደር ተመድቦ ለጥያቄያቸው መልስ እንዲሰጥ ተወሰነ ፡፡ በተጨማሪም ፤ የሙያ ትምህርት ያልነበራቸው  ሁሉ በመከላከያ ሠራዊት እያሉና ያገልግሎት ጊዜያቸውን አጠናቀው ከሠራዊቱ ሲለቀቁ የሚጠቀሙበት የሙያ ሥልጠና ዕድሎች ይሰጣቸዋል ፡፡ ግዳጃቸውን አጠናቀው ከሠራዊቱ ሲለቀቁ ምን ዕይነት መብቶች እንዳሏቸውና ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፤ ለምሳሌ በሥራና በሌሎችም ጉዳዮች ምክራዊ እርዳታወች ይቀበላሉ ፡፡