በሱዳን በኩል እሥራኤል ለመድረስ በመንገድ ሳሉ ህይዎታቸው ያለፈ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች መታሰቢያ ቀን - የኢትዮጵያ አይሁዲ ቅርስ ማዕከል

በሱዳን የሞቱት ወገኖች

ወደ እስራኤል (እየሩሳለም) ለመምጣት በመንገድ ላይ ሳሉ ሕይወታቸው ያልፈ የኢትይጵያ ይሁዲወች የሙታን መታሰቢያ ቀን

ይህ ቀን ሕልማቸውና ምኞታቸው እዉን ሳይሆንላቸው ወደ እየሩሳሌም በመንገድ እያሉና ሱዳን ዉስጥ ሕይወታቸው ያለፈው፤ እሴት ወንድ፤ አዛውንት ፤ ታዳጊ ልጆችና ህጻናት የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡ ይህ ቀን ለኢትጵያ ይሁዲወች በጣም ከባድና የሃዘን ቀን ነው ፤ በተለይ ቤተ ሰብ ለሞተባቸው ፡፡
የሙታን መታሰቢያው ቀን እየሩሳሌም በተዋሃደችበት ቀን እንዲሆን የተወሰነበት ምክያት አለው ፡፡ ከትውልድ እስከ ትውልድ ለብዙ ሽህ ዓመታት ሲያልሟት የኖሩት እየሩሳሌም የተዋሃደችበት ቀን ስለሆነ፤
በዚህ የሙታን መታሰቢያ ቀን የትዮጵያ ይሁዲወች፤ እስራኤል በሚኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ ይዘከሩታል ፡፡ትልቁ የሙታን መታሰቢያ ቀን በመንግስታዊ ደረጃ እየሩሳሌም በሃር ሄርጽል ሲሆን ፤ መንግሥታዊ ባለስልጣናት፤ የሙታን ቤተ ሰቦችና ዘመዶች እንዲሁም ሌላ የሥራኢል ህብረተ ሰብ አባላት ይሳተፉበታል፤፡፡

ያለፉት አጋጣሚዎች

May 18
በሱዳን በኩል እሥራኤል ለመግባት በመንገድ ሳሉና ሱዳን ውስጥ የሂዎት ምስዋዕትነት ለከፈሉት ቤተ እሥራኤላውያን ወገኖቻችን በመንግሥት ደረጃ የሚካሄደው የመዘከር ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ስርጭት።

በሱዳን በኩል እሥራኤል ለመግባት በመንገድ ሳሉና ሱዳን ውስጥ የሂዎት ምስዋዕትነት ለከፈሉት ቤተ እሥራኤላውያን ወገኖቻችን በመንግሥት ደረጃ የሚካሄደው የመዘከር ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ስርጭት።

18.05.2023 11:00