ארכיון Events - የኢትዮጵያ አይሁዲ ቅርስ ማዕከል

Events

Filter by event type
Filter by year
June 05
እስራኤል ለመድረስ በሱዳን ጉዞ ሞተው ለቀሩት የኢትዮጵያ ይሁዳውያን መንግስታዊ መታሰቢያ ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ስርጭት

እስራኤል ለመድረስ በሱዳን ጉዞ ሞተው ለቀሩት የኢትዮጵያ ይሁዳውያን መንግስታዊ መታሰቢያ ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ስርጭት

Herzl's Grave, Mount Herzl Cemetery, Jerusalem
05.06.2024 11:00 - 13:00
April 16
የቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ

የቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ

16.04.2024 17:00 - 20:00
የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል ማዕከል፣ በቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ ይሳተፉ  ዘንድ ይጋብዝዎታል   ዕለተ ማክሰኞ  ኔሳን 8 ቀን 16.4.2024 በ 17፡00 ሰዓት   ኤሽኮል 2 አዳራሽ ቢንያኔ ሃኡማ ሻዛር ጎዳና ቁ. 1 እየሩሳሌም   በምረቃው ስነሥርዓት ሊቃ ካህናት  ብርቁ፣ ቄሶች፣ የሕዝብ ተወካዮች እና ሰፊው ማሕበረሰብ ይገኙበታል።   የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት በሁለት ጥራዞች ይከፈላሉ   1 - የአቪቭ ወራት በዓላት፣ የኔሳን፣ ፋሲካ እና የሰኔ ማእረር 2 - የሰባተኛው ወር በዓላት፤ ብርሃን ሠረቀ፣ በዓለ መጸለት እና የህዳር ማእረር   መጽሐፉን አሰባስበው የጻፉት ካህን ምንተስኖት ማሙ ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል ማዕከል አርሞ ለምረቃ አዘጋጅቷል።   የተሳትፎ ገደብ ስላለው፣ ቅድመ ምዝገባ ያስፈልጋል።   እንጠብቅዎታለን ዝግጅቱ በካሜራ ይቀረጻል
November 13
የስግድ ጸሎት በእየሩሳሌም

የስግድ ጸሎት በእየሩሳሌም

በእየሩሳሌም አርሞን ሀናጺቭ መናፈሻ ተራራ
13.11.2023 09:30 - 13:00
አገራችን ባለችበት "የብረት ሰይፎች" ጦርነት ምክንያት እና በደጀን እዝ (ፒኩድ ሀዖሬፍ) መመርያ መሰረት፣ የስግድ ጸሎት በካህናት ተሳትፎ ብቻ በእየሩሳሌም አርሞን ሀናጺቭ መናፈሻ ተራራ ይካሄዳል፡፡   ማህበረሰቡ በየአለበት ቦታ ጸሎቱን እንዲከታተል፣ ከእየሩሳሌም በቀጥታ ስርጭት በኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል እና ቅርስ ማእከል ድረ-ገጽ፣ ዩቲዩብ እና ፌስቡክ   ከ 9፡30 እስከ 13፡00 ሰዓት መከታተል ይችላል።   ከጸሎቱ በኋላ የክብር እንግዶች ንግግር አይደረግም፡፡ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ፣ በኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል እና ቅርስ ማእከል፣ በካህናት-የሐይማኖት አመራር እና የክብረ በዓላት እና መንግስታዊ ዝግጅቶችን አቀናባሪ ክፍል ተዘጋጀ
May 18
በሱዳን በኩል እሥራኤል ለመግባት በመንገድ ሳሉና ሱዳን ውስጥ የሂዎት ምስዋዕትነት ለከፈሉት ቤተ እሥራኤላውያን ወገኖቻችን በመንግሥት ደረጃ የሚካሄደው የመዘከር ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ስርጭት።

በሱዳን በኩል እሥራኤል ለመግባት በመንገድ ሳሉና ሱዳን ውስጥ የሂዎት ምስዋዕትነት ለከፈሉት ቤተ እሥራኤላውያን ወገኖቻችን በመንግሥት ደረጃ የሚካሄደው የመዘከር ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ስርጭት።

18.05.2023 11:00
November 23
የስግድ በዓል በእየሩሳሌም 2022

የስግድ በዓል በእየሩሳሌም

ቦታውም በኢየሩሳሌም አርሞን ሃናጺብ አጠገብ በሚገኘው ታየሌት ሽሩበር በተባለው መናፈሻ ቦታ ነው
23.11.2022 08:00 - 14:00
በእየሩሳሌም ከተማ በሚካሄደው የስግድ በዓል ማዕከላዊ የጸሎት ስነ ስርዓት አከባበር እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል በዓሉ የሚከበረው ረቡዕ ህዳር(ኖቬምበር) 23 ቀን 2022 ዓ/ም ካፍ-ቴት በሄሽቫን- ታፍ-ሺን-ፔ-ጊሜል ሲሆን ቦታውም በኢየሩሳሌም አርሞን ሃናጺብ አጠገብ በሚገኘው ታየሌት ሽሩበር በተባለው መናፈሻ ቦታ ነው የጸሎቱ ስነ ሥራዓት መድረክ በ 8፡00 ሰዓት ይጀምራል የበዓሉ መንግሥታዊው አከባበር በ12:30 ሰዓት ይካሄዳል በዚሁ ቀን ከእየሩሳሌም አውቶቡስ ጣቢያ(ታሃና መርካዚት) ዝግጅቱ ወደሚከናወንበት ቦታ የሚወስዱ ልዩ የህዝብ ማጓጓዣዎች ተዘጋጅተዋል:: በተጨማሪም ከመላው ሀገሪቱ ወደ እየሩሳሌም የሚወስዱ አውቶብሶችም ተዘጋጅተዋል:: የአውቶቡሶችን መነሻ ጊዜ እና ቦታ ለማወቅ በአካባቢ ያሉትን መስተዳድሮች በመጠየቅ ወይም የማስታወቂያ ክፍል ቢሮ ድረ ገጽ በማየት ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል:: https://www.gov.il/he/departments/hq-for-state-ceremonies-and-events