የቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ - የኢትዮጵያ አይሁዲ ቅርስ ማዕከል
የቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ

የቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ

16.04.2024 17:00 - 20:00

የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል ማዕከል፣ በቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ ይሳተፉ  ዘንድ ይጋብዝዎታል

 

ዕለተ ማክሰኞ  ኔሳን 8 ቀን 16.4.2024 በ 17፡00 ሰዓት

 

ኤሽኮል 2 አዳራሽ ቢንያኔ ሃኡማ ሻዛር ጎዳና ቁ. 1 እየሩሳሌም

 

በምረቃው ስነሥርዓት ሊቃ ካህናት  ብርቁ፣ ቄሶች፣ የሕዝብ ተወካዮች እና ሰፊው ማሕበረሰብ ይገኙበታል።

 

የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት በሁለት ጥራዞች ይከፈላሉ

 

1 - የአቪቭ ወራት በዓላት፣ የኔሳን፣ ፋሲካ እና የሰኔ ማእረር

2 - የሰባተኛው ወር በዓላት፤ ብርሃን ሠረቀ፣ በዓለ መጸለት እና የህዳር ማእረር

 

መጽሐፉን አሰባስበው የጻፉት ካህን ምንተስኖት ማሙ ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል ማዕከል አርሞ ለምረቃ አዘጋጅቷል።

 

የተሳትፎ ገደብ ስላለው፣ ቅድመ ምዝገባ ያስፈልጋል።

 

እንጠብቅዎታለን

ዝግጅቱ በካሜራ ይቀረጻል