ארכיון Events - የኢትዮጵያ አይሁዲ ቅርስ ማዕከል

Events

Filter by event type
Filter by year
November 20
የስግድ በዓል በእየሩሳሌም
ፎቶግራፉን ያነሳ: አርኑን ቡሳኒ

የስግድ በዓል ጸሎት በእየሩሳሌም

Sherover Promenade near Armon Hanatziv, Jerusalem.
20.11.2025 08:00 - 14:00
በእየሩሳሌም ከተማ በሚካሄደው ማዕከላዊ የስግድ በዓል ጸሎት ሥነ ሥርዓት አከባበር እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል ሐሙስ ቀን 20/11/2025 ካፍ ጤት በሔሽቫን ታፍ-ሺን-ፔ-ቫቭ በኢየሩሳሌም፣ አርሞን ሃናጺብ አጠገብ በሚገኘው ታየሌት ሽሩበር መናፈሻ ቦታ ነው   በ 8፡00 የጸሎቱ ቦታ ይከፈታል በ 12፡30 ቡራኬ እና መንግሥታዊ የክብር ሥነ ሥርዓት በ 14፡00 የጸሎት እና የፆም መጨረሻ   በዚሁ ቀን ከእየሩሳሌም ሻዛር ጎዳና ቢንያኔ ሃኡማ አጠገብ ወደ ዝግጅቱ ቦታ የሚያደርሱ የመጓጓዣ አውቶቡሶች ይሰማራሉ። በተጨማሪም ከመላው ሀገሪቱ ወደ እየሩሳሌም የሚወስዱ አውቶብሶችም ተዘጋጅተዋል:: ለተጨማሪ መረጃ፡ በኢሜል info@moreshete.org.il ስልክ 02-6772568
May 26
ወደ እስራኤል (እየሩሳለም) ለመምጣት በመንገድ ላይ ሳሉ ሕይወታቸው ያልፈ የኢትይጵያ ይሁዲወች የሙታን መታሰቢያ ቀን

እስራኤል ለመድረስ በሱዳን ጉዞ ሞተው ለቀሩት የኢትዮጵያ ይሁዳውያን መንግስታዊ መታሰቢያ ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ስርጭት

Herzl's Grave, Mount Herzl Cemetery, Jerusalem
26.05.2025 11:00 - 13:00
November 28
የስግድ በዓል በእየሩሳሌም
ፎቶግራፍ፡ DMD

የስግድ በዓል በእየሩሳሌም

በኢየሩሳሌም፣ አርሞን ሃናጺብ  አጠገብ በሚገኘው ታየሌት ሽሩበር መናፈሻ ቦታ ነው
28.11.2024 08:00 - 14:00
በእየሩሳሌም ከተማ በሚካሄደው ማዕከላዊ የስግድ ጸሎት ሥነ ሥርዓት አከባበር እንዲሳተፉ  በአክብሮት ተጋብዘዋል ሐሙስ ቀን 28/11/2024  ካፍ ዛይን በሔሽቫን ታፍ-ሺን-ፔ-ሄይ በኢየሩሳሌም፣ አርሞን ሃናጺብ  አጠገብ በሚገኘው ታየሌት ሽሩበር መናፈሻ ቦታ ነው   በ 8፡00 ሰዓት የጸሎቱ ቦታ ይከፈታል በ 12፡30 ሰዓት ቡራኬ እና መንግሥታዊው አከባበር በ 14፡00 የጸሎት እና የፆም መጨረሻ   በዚሁ ቀን ከእየሩሳሌም ሻዛር ጎዳና ቢንያኔ ሃኡማ አጠገብ ወደ ዝግጅቱ ቦታ የሚያደርሱ የመጓጓዣ አውቶቡሶች ይሰማራሉ። በተጨማሪም ከመላው ሀገሪቱ ወደ እየሩሳሌም የሚወስዱ አውቶብሶችም ተዘጋጅተዋል:: ለተጨማሪ መረጃ፡ በኢሜል info@moreshete.org.il ስልክ 02-6772568  
June 05
እስራኤል ለመድረስ በሱዳን ጉዞ ሞተው ለቀሩት የኢትዮጵያ ይሁዳውያን መንግስታዊ መታሰቢያ ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ስርጭት

እስራኤል ለመድረስ በሱዳን ጉዞ ሞተው ለቀሩት የኢትዮጵያ ይሁዳውያን መንግስታዊ መታሰቢያ ሥነ ሥርዓት የቀጥታ ስርጭት

Herzl's Grave, Mount Herzl Cemetery, Jerusalem
05.06.2024 11:00 - 13:00
April 16
የቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ

የቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ

16.04.2024 17:00 - 20:00
የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል ማዕከል፣ በቤተ እስራኤል የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት ምረቃ ይሳተፉ  ዘንድ ይጋብዝዎታል   ዕለተ ማክሰኞ  ኔሳን 8 ቀን 16.4.2024 በ 17፡00 ሰዓት   ኤሽኮል 2 አዳራሽ ቢንያኔ ሃኡማ ሻዛር ጎዳና ቁ. 1 እየሩሳሌም   በምረቃው ስነሥርዓት ሊቃ ካህናት  ብርቁ፣ ቄሶች፣ የሕዝብ ተወካዮች እና ሰፊው ማሕበረሰብ ይገኙበታል።   የበዓላት ጸሎት መጽሐፍት በሁለት ጥራዞች ይከፈላሉ   1 - የአቪቭ ወራት በዓላት፣ የኔሳን፣ ፋሲካ እና የሰኔ ማእረር 2 - የሰባተኛው ወር በዓላት፤ ብርሃን ሠረቀ፣ በዓለ መጸለት እና የህዳር ማእረር   መጽሐፉን አሰባስበው የጻፉት ካህን ምንተስኖት ማሙ ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል ማዕከል አርሞ ለምረቃ አዘጋጅቷል።   የተሳትፎ ገደብ ስላለው፣ ቅድመ ምዝገባ ያስፈልጋል።   እንጠብቅዎታለን ዝግጅቱ በካሜራ ይቀረጻል
November 13
የስግድ ጸሎት በእየሩሳሌም

የስግድ ጸሎት በእየሩሳሌም

በእየሩሳሌም አርሞን ሀናጺቭ መናፈሻ ተራራ
13.11.2023 09:30 - 13:00
አገራችን ባለችበት "የብረት ሰይፎች" ጦርነት ምክንያት እና በደጀን እዝ (ፒኩድ ሀዖሬፍ) መመርያ መሰረት፣ የስግድ ጸሎት በካህናት ተሳትፎ ብቻ በእየሩሳሌም አርሞን ሀናጺቭ መናፈሻ ተራራ ይካሄዳል፡፡   ማህበረሰቡ በየአለበት ቦታ ጸሎቱን እንዲከታተል፣ ከእየሩሳሌም በቀጥታ ስርጭት በኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል እና ቅርስ ማእከል ድረ-ገጽ፣ ዩቲዩብ እና ፌስቡክ   ከ 9፡30 እስከ 13፡00 ሰዓት መከታተል ይችላል።   ከጸሎቱ በኋላ የክብር እንግዶች ንግግር አይደረግም፡፡ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ፣ በኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባህል እና ቅርስ ማእከል፣ በካህናት-የሐይማኖት አመራር እና የክብረ በዓላት እና መንግስታዊ ዝግጅቶችን አቀናባሪ ክፍል ተዘጋጀ