የምርምርና ጥናት ተቋም
ተቋሙ በቋሚ ሠራተኞቹ አማካኝነትና በዉጭ ተመራማሪወች ትብብር ስለ ኢትዮጵያ ይሁዲወች ምርምሮችና ጥናቶች ሥራ ያካሄዳል ፡፡ ያሉትን የጥናት ውጤቶችም ሰፊው ሕዝብ እንዲጠቀምበት በማድረግ ፤ ስለ ኢትዮጵያ ይሁዲወች የተለያዩ አዳዲስ የጥናት ውጤቶችን ለሚያሳዩ ምስጉን ስቱደንቶችና ተመራማሪወች የገንዘብ እርዳታ ይሰጣል ፡፡
የኢትዮጵያ ይሁዲወችን ባስመለከተ ተቋሙ በየዓመቱ ጉባኤ ያደርጋል፤ በተለያዩ ርዕሶች ያተኮረ ፤ ለምሳሌ ስለ ሥግድ በዓል ፤ ሚብጻ ሽሎሞና ሚብጻ ሞሸ የተጠናቀቁበትን ቀን አስመልክቶና ሌሎችንም፡፡ በተጨማሪም የተልያዩ አስተማሪወች ለሰፊው ሕዝብ ያለ ክፍያ በዙም ትምህርታዊ ገለጻወች ይሰጣሉ ፡፡ የተቀርጹ የትምህርት ዓይነቶችን በተቋማችን ዩቲውብ አማካኝነት ማዳመጥም ይቻላል፡፡