ስለኢትዮጵያ ይሁዲዎች
ይሁዲዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ሂደው ስለመኖራቸው ፡፡
የኢትዮጵያ ይሂዲዎች ታሪክ እንዴት እንደ ነበር እስክ 14/ ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በጽሁፍ የተጋጀ በቂ መረጃ አልተገኘም፤ በቃል ከትውልድ ወደ ትዉልድ የተላለፈ ነው እንጅ ፡፡ ስለዚህ የኢትዮጲያ ይሁዲዎች ከየት ተነስተውና መቸ እንደሄዱ በትክክል ማወቅ አልተቻለም፡፡ስለዚህ ሁኔታ ለበዙ አመታት የተለያዩ አመልካከቶች ሲጠቀሱ ቆይተዋል፡፡
1/ ቤተ ስራኤል በሚል ስማቸው የሚታዎቁት ይሁዲወች መነሻ ፤ ከነገደ ዳን ሆኖ የእስራል ነገሥታት ሲከፋፈሉ አሥሩ ነገደ እስራኤል ለስደት በወጡበት ጊዜ ፤ ወይም ጥቂት ቀደም ብሎ ነው የሚል ግምትም አለ ፡፡ ይሁዳውያን ስደተኞች ኩሽ ከምትባል አገር የሚገኙ ለመሆናቸው ከነቢያት መጽህፍት እናገኛለን ፡፡ " በዚያም ቀን እግዚአብሄሔር ኅይሉን አሳየ ፤ እጁን ዘርግቶ የቀረውን ሕዝቡን ለአህዛብ ታኣምር በማሳየት፤ ከእሥር፤ ክግብጽ፤ ኩሽና ፓትሮስ በስደት የሚኖሩትን የይሁዳ ሰደተኞች ከአራቱ የምድር ማዕዘን ይሰበስባል ( (ትንቢተ ኢሳያስ መዕራፍ 11 ቁጥር 11 እስከ 12 ) የኢሳያስ መጽሐፍ እነዚህን ነገዶች ከዳን ነገድ ጋር አያዛምዳቸውም ፤ በ9/ኛው ክፍለ ዘመን ኤልዳድ ሃዴኒ የሚባለው ነው ከዳን ነገድ ጋር ያዛመዳቸው፤ ቆየት ብሎም ከራባናት፤ እንደ ራድባዝ ካሉት ምንጮች ይገኛል፤ እነዚህን ምንጮች መሠርት በማድረግ ነው የእስራኤል ሊቀ ራባናት የነበሩት ኦቫዲያ ዮሴፍ ፤ የኢትዮጲያን ይሁዲዎች እዉነተኛ ይሁዲዎች ናቸዉ ብለው የወሰኑት፡፡
2/ በተለያዩ ዘመናት ከልደት በፊት ከ9/ ኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ ግብጽ ውስጥ በመካከላቸው በተፈጠረ መከፋፈልና በሌሎች ጥላቻ መክኒያት ፈልሰው የተሰደዱ ናቸው ተብሎም ይገመታል ፤ ይህ ግምት በኢትዮጲያ ይሁዲዎች በኩልም ተቀባነት ያለው ሲሆን የኢትዮጲያ ይሁዲዎች ታሪክ ተመራማሪዎችም ያምኑበታል የብ ( ኤሌፋንቲና) ይኖሩ ከነበሩት የጥንት ይሁዲዎች ባህልና የቤተ እሥራኤሎች ባህል መካከል ብዙ ተመሳሳይ የሆኑ ልምዶች ስለተኙ ፡፡
3/ የቤተ እስራኤሎች የጥንት አባቶች ከግብጽ ሳይሆን ከደቩቭ መዕራብ ( ከየመን) የሄዱ ናቸው የሚሉም አሉ፤ ካገሩ በርካታ ይሁዲዎች ስለነበሩ፤ ይህ አባቫል በበርካታ ተመራማሪወችም ተቀባይነት ሊያገኝ የቻለበት ምክኒያት፤የሁልቱ አገሮች መልካአ ምድር
የተቀራራበ በመሆኑና ከአምስተኛው ዓመተ ዓለም ጀምሮ በሁለቱ አገሮች መካከል የንግድና የባህል ግንኙነት ስለነበረ ነው ይላሉ ፡፡
4/ እንደ ኢትዮጵያውያን ብሄራዊ እምነት ፤ የመጀመሪያ ይሁዲዎች ኢትዮጵያ የመጡት በሰለሞን ዘመነ መንግስት ጊዜ እንደ ሆነ አድርገው ነው፡፡ ይህ አባባል መሠረት የሚያደርገው ከመጽሓፍ ቅዱስ የሚተረከውን የንግሥተ ሳባና ንጉሥ ሰለሞን መገናኘትና ምኒሊክ የሚባል ልጅ ከመወለዱ ጋር በማያያዝ ነው፤ ምኒልክም ኢትዮጵያ አድጎ ፤ ለአቅመ አዳም ሲደርስ አባቱን ለማየት ወደ እየሩሳሌም ይሄድል፤እየሩሳሌም ከአባቱ ጋር ከተገናኘ በኋላ ወደ እናቱ አገር ሲመለስ አባቱ ከነገደ እስራኤል ሰዎች መካከል አጅበውት እንዲሄዱ አደርገ ፤ እነዚህ ናቸው የኢትዮጲያ ይሁዲዎች ተብሎ በሰፊው ይታመንበታል፡፡
5 / የኢትዮጵያ ይሁዲዎች መነሻ ከቀደምት ይሁዲዎች ሳይሆን ከ14/ኛው እስከ 15/ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ የይሁዲ ሃይማኖትን የተቀበሉት በጊዜው ኢትዮጵያ የነበሩት የአገው ህብረተ ሰብ አባል ናቸው የሚሉም አሉ፡፡ይህ አባባል በተለያዩ ተመራማሪዎች በኩል ትኰረት ሲሰጠው ይስተዋላል፤ ምክኒያቱም ከ14/ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነው ይሁዲዎች ኢትዮጵያ ስለመኖራቸው በነገሥታት ዜና መዋእል ተጠቅሶ የሚገኝ ፡፡ ይህን አባባል ቤተ እሥራኤሎች ፈጽሞ አይቀበሉትም፡፡ አብዛኛወች ተመረማሪዎች የሚሉት ክርስትና ኢትዮጵያ ከመድረሱ በፊት በቀደምት ጊዜ ነው ይሁዲዎች ኢትዮጵያ የነበሩት ይላሉ፡፡
እስከ 19/ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጲያ ይሁዲዎች ታሪክ
ቀደም ሲል እንደተጠቀስው፤ ከ14/ኛው ክፍለ ዘመን በፊት የነበረው በቃል ብቻ የሚተረክ በባህላዊ አፈ ታሪክ ነው የነበረ ፡፡ አንዱ መሰረታዊና ባህላዊ ታሪክ ሆኖ ያለው የጊድኦን ሥርዎ መንግስት ተብሎ በሚታወቅው ዘመን ይሁዲዎች እትዮጵያን ለብዙ ዓመታት ያስተዳደሯት ስለመሆኑ ነው፡፡ ከነዚህ መሪወች መካከልም በ 10/ኛው ክፍለ ዘመን የአማጺያን አዛዥ የነበረችው ደፋርና ጨካኝ ተብላ የምትጠራውና ለ 40 ዓመታት የገዛችው ይሁዲት ስትሆን ፤ በግዛት ዘመኗ ጊዜ አክሱም የነበረውን የክርስቲያን ኅይል አንኮታኮተችው፡፡ ይሁዲዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ የራሳቸው ነጻ ሃገርና መንግስት መሥርተው ስለመኖራቸው በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ነው ለአውሮፓዉያን ወሬው የደረሳቸው፡፡ ቀደም የተጠቀሰው ኤልዳድ ሃዴኒ እና እንዲሁም ተጓዡ ቤንያሚን ሜቱዴላ እና ሌሎችም ከጻፉት ነው ይሁዲዎች ኢትዮጵያ ስለመኖራቸው ማወቅ የተቻለ ፡፡
ስለ ኢትዮጵያ ይሁዲወች በጽሁፍ የተረጋገጡ መረጃወች የተገኙት ከኢትዮጵያ የነግሥታት ዜና መዋዕል ነው፡ ከ14/ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የኢዮጵያ ይሁዲወች ሃይማኖታቸውንና ነጻነታቸውን ለመጠበቅ ከክርስቲያን መንግስት ጋር ስለካሄዷቸው ከባድ ጦርነቶች የነገሥታት ገድል ያስረዳል፡፡ ይሁዲዎች ጨርሰው እስኪሸነፉ በጭካኔ የተዋጋቸው ንጉስ ይስሓቅ ነበር ፤
ባሸነፈበት ጊዜም ንጉሡ ስለይሁዲዎች ለዩ ትዕዛዝ አወጣ፡፡ " የክርስትና ሃይማኖት የማይቀበል ሁሉ የመሬት ባለቤትነት አይኖረውም " የሚል፤ አብዛኛዎች ይሁዲወች ሃይማኖታቸን አንቀይርም ስላሉ የመሪት ባለቤትነት መብታቸዉን ተነጠቁ ፡፡ የመሪት ተጠማኞች ሆኑ፤ በዚህ ምክኒያት ሌላ አማራጭ የሆነ የገቢ ምንጭ ፈጠሩና ፤ ወንዶች በብረት ሥራና በልብስ ሽመና ሥራ ፤ እሴቶች በሸክላና ልብስ እየጠለፉ በማስጌጥ ሥራ ተሠማሩ ፡፡ የዚህ ዓይነት ዕደ ጥበብ ሥራ በአካባቢ በሚገኙት ክርስቲያኖች በኩል ከባድ የሆነ ጥላቻ አስከተልባቸው፡፡ በነሱ አስተሳሰብና አመለካከት የዚህን ዓይነት ሥራ የተናቀና የተንቋሸሸ ሥራ አስመስለው ቆጠሩት ፡፡ ብረት መሥራትን እንደ አስማተኛነት ነበር የሚቆጠሩት ፡፡ የሁዲዎችና የክርስቲያኖች ጦርነት እስከ 17/ኛው ክፍለ ዘመን ነበር የቀጠለ ፡፡ ያኔ ግን የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ለአንዲና ለመጨረሻ ጊዜ ነጻነታቸውን አጡ፡፡
1888_ 1892 ዓ/ም በኢትዮጵያ ላይ ከባድ የሆነ ጥፋት የደርስበት ዘመን ነበር ፡፡ በቤት እሥራኤሎች ላይም ከባድ ጉዳት አስከትሏል፤ በዚህ " ክፉ ቀን " ተብሎ በሚጠራው ዘመን ሌላ ተከታታይ ርሃብና ወረርሽኝ በሽታ ያስከተለ ፡ የተፈጥሮ አዳጋወችና ጦርነቶች የተፈራረቁበት ዘመን ነበር ፤ በዚህ የክፉ ቀን ዘመን ከኢትዮጵያ ይሁዲወች መካከል ከሶስት እጅ እስከ ሁለት ሶስተኛ እጅ የሚሆኑት አልቀዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ዉጭ ከሚኖሩት ይሁዲወች ጋር ግንኙነቱ
የኢትዮጵያ ይሁዲወች ከተስደዱበት ቀን ጀምሮ ለበርካታ ዓመታ ከሌላው ከፍለ ዓለም ይኖሩ ከነበሩት ይሁዲወች ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራችውም ፡፡ በ19/ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ነው ግንኙነቱ የታደሰ ፤ የኤውሮፓዉያን አገራት ጎብኝዎችና ክርስትና ሰባኪ ሚሲዮኖች ናቸው ይሁዲዮች ኢትዮጵያ ስለመኖራቸው ባዘጋጁት ጽሁፍ ለኤዉሮፓውያን ያሳውቁት፡፡ በመጀመሪያ ግንኙቱ የተፈጠረ በቀጥታ አልነበረም፡፡ ደብዳቤወች በመላላክ በቻ ነበር፤ በ1855 ዓ/ም ነበር የምጀመሪዉ ቀጥተኛ የሆነ መገናኘት የተፈጠር፡፡ የኢትዮጵያ ይሁዲወች አባል የሆነ ዳኒኤል ቤን ሃናኒያ የሚባል ከልጁ ጋር ሆኖ እየሩሳለም ሂዶ ፤ እየሩሳሌም ከሚኖሩት ራባት ጋር ለተወሰኑ ወራት ከተቀመጠ በኋላ ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡
በሌላ ከፍለ ዓለም ከሚኖሩት ይሁዲወች ጋር መጠነኛ የሆነ መገናኘት ስለተፈጠረና ሚሲዮኖች የስበካ ስራቸዉን እያጠናከሩ መሆናቸውን በሌላ ዓለም የሚኖሩት ይሁዲወች ሲሰሙ ልዩ መልዕክተኛ ወደ ኢትዮጵያ ሰደው ሁኔታውን ማወቅ ፈለጉ ፡፡ የመጀመሪያው መልዕክተኛ ዮሴፍ ሃሌቪ ነበር፤ በ1867 ዓ/ም ኢትዮጵያ ደርሰ፡፡ ከ 30 ዓመት በኋላ የሱ ተማሪ የሆነው
ያዓቆቭ ፋይትሎቪች ነው ስለ ኢትዮጵያ ይሁዲወች ጉዳይ በሌላ ዓለም ከሚኖሩት ይሁዲዎች ጋር በማስተዋዎቅና በመሥራት ሙሉ ሕይወቱን አሳለፈ፡፡ የርሱ ተልዕኮ በመላው ዓለም እየተዘዋወረ የኢዮጵያ ይሁዲወችን ማንነት ማስተዋወቅ ፤ ገንዘብ ማሰባሰብ ፤ የሰባኪ ሚሲዮኖችን ስራ ማክሸፍና ትምህርት ቤቶች ማቋቋም ነበር ፡፡ ከኢአትዮጵያ ይሁዲዎች መካከል
የተወሰኑ ወጣቶች ተመርጠው ለትምህርት ወደ ኤዉሮፓ ተላኩ ፡፡ ተምረው ከተመለሱት መካከል ከፊሎች በኢትዮጵያ መንግስት በከፍተኛ ሥልጣን ተሾሙ ፡ ሌሎች የቤተ እሥራኤሎች ሃላፊ ሆነው አገለገሉ ፡፡ ከነዚህ መካከላቸውም ታምራት አማኑኤል፤ ጌጤ ኤርሚያስ ፤ ዮና ቦጋለና ታደሰ ያዕቁብ ናቸዉ፡፡
ከ20/ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ አንስቶ በኢትዮጵያ ይሁዲወችና በአለም ጺዮናውያን መሪዎች መካከል ገንኙነቱ እየጠነከረ ሄደ ፡፡ ለምሳሌ በ 50 ዎች ዓ/ም አካባቢ በሁለት ዙር የቤተ እሥራኤል ወጣቶች ለተወስኑ ዓምታት ክፋር ባቲያ ከሚባለው አዳሪ ት/ም ቤት እንዲማሩ ተወስድዋል፤ ተምረው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የቤት እሥራኤልን ልጆች አስተማሩ፡፡ ሰለሆነም እስከ 1970 ዓ/ም ቤተ እሥራኤሎች ወደ እስራኤል እንዲመጡ በመንግስት በኩል ምንም አይነት ጥረት አልተደረገም ፡፡
ወደ እስራኤል መምጣት
ቤተ እሥራኤሎች ወደ እሥራኤል ለመመልስ የነበራቸው ጉጉትና ፍላጎት ሁልጊዜም የጸና ነበር ፡፡ ይህን ጉጉታቸውንና ፍላጎታቸውን በጸሎታቸውና በዝማሬያችው፤ በሥግደትና በሥግድ በዓልም ይገልጹት ነበር፡፡ በ1862 ዓ/ም የቤተ እስራኤል መነሳዊ መሪ የሆኑት አባ ምሃሪ ይህን ከፍተኛ ጉጉት ተግባራዊ ለማድረግ ወገኖቻቸውን " ተከተሉኝ ቀይ ባሕርን አቋርጠን እየሩሳሌም ለንገባ ነው " ብለው በመቀስቀስ መንገድ ጀመሩ፡፡ ሙከራው ሳይሳካላችው ቀረ፤ ብዙ ጉዳትም ደረሱባቸው፤ ብዙወች ሞቱ የተረፉት ጥቂቶችወደ ነበሩበት ተመለሱ ፡፡
እስራኤል ከመቋቋሟ በፊትና ከተመሠረተች በመጀመሪው አሥር ዓምት ዉስጥ አንዳንድ ቤተ እሥራኤሎች መጥተዋል ፡፡ ከፊሎች ከየመን ይሁዲወች ጋር ተጋብተው ፡፡ ይሁን እንጅ የእሥራኤል መንግሥት የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ለማምጣት መንም አይነት ሙከራ አላደረገም፤ ቤት እሥራኤሎች ትክክልኛ ይሁዲ መሆናቸውን የሃገሪቱ መሪዎች የመቀበል ፍላጎት ስላልነበራቸው ፡፡፤ በዚህ መክኒያትም ቤተ እሥራኤሎች ወደ እሥራኤል የመምጣት ዕድል ማግኘት አልቻሉም ፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ቤተ እሥራኤሎች ቢመጡ እሥራኤል ከሚኖሩት ጋር በማህብራዊና በባህል ዘርፎች ተግባብተው መኖር ይከብዳቸዋል ይሉ ነበር ፡፡
የዚህ ዓይነት ጥርጣሪዎች በሁገሪቱ መሪወች በኩል ቢፈጠሩም አንዳንድ የቤተ እሥራኤል ወጣቶች አገር ጎብኝዎች ወይም ሥራ ፈላጊወች መስለው እሥራኤል የገቡም አሉ ፡፡ ከፊሎች እዉነትኛ ይሁዲዎች መሆናችሁ አስተማማኝ አይደለም ተብለው ድጋሜ ግርዛት ለማድረግ ተገደው ከፈጸሙ በኋላ የአዲስ ገቢነት መብት ማግኘት ሲችሉ ሌሎች ግን ከህግ ውጭ በሃገሪቱ በመኖር ላይ ናቸሁ ተብለው በአስቸኳይ ከእሥራኤል እንዲባረሩ ተዛዝ ተሰጣቸው፡፡ ቤተ እስራኤሎች በእስራኤል መግሥት ላይ በፈጠሩት ተጽዕኖ ምክኒያት በወቅቱ
የእስራኤል ሊቀ ራባናት የነበሩት ራብ ኦባዲያ ዮሴፍ በ 1973 ዓ/ም ቤተ እስራኤሎች እውነተኛ ይሁዲዎች ናቸው የሚል ሃይማኖታዊ ውሳኔ አስተላለፉ ፡፡ ይህን ውሳኔ የእስራኤል መንግስት ወዲያውኑ ተግባራዊ ሳያደርግ ከቆየ በኋላ በ1975 ዓ/ም ወደ እስራኤል መመለስ መብት ያለው ማነው የሚልው አጠቃላይ ሕግ ለቤተ እስራኤሎችም የሚያገለግል መሆኑ ጸደቀ ፡፡ ቢሆንም ይህ ውሳኔ በተግባር ላይ እንዲዉል የስራኤል መንግስት አልተቻኮለም ፡፡ እስከ 1977 ዓ/ም ቁጥራቸው 200 የሚሆኑ በተ እስራኤሎች ብቻ እስራኤል ይኖሩ ነበር፡፡
እነዚህ ቁጥራችው አነስተኛ የሆኑት ቤተ እስራኤሎች ለውጥ ለማምጣት ቆርጠው በመነሳሳት አቤቱታወችን ፤ በስላምዊ ሰልፎችና ከተለያዩ ሰወች ጋር እየተገናኙ ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሃገራት ከሚገኙ ባለሥልጣናት ለጥያቄያቸው ድጋፍ ጠየቁ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ጥያቄ ለመደገፍ በተመሠረተው የአሜሪካ ይሁዲወች
ማህበር (AAEJ ) እርዳታ የቤተ እስራኤሎችን ወኪሎች ወደተለያዩ አገሮች እየወሰዱ በመላው ዓለም የሚገኙ መንግስታትና የይሁዳውያን ድርጅቶች በእስራኤል መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ የተጠናከረ ሥራ አካሄዱ ፡፡
ምናሄም ቤጊን የእሥራኢል ጠቅላይ ሚኒስትር ሁነው ሲመረጡ ነው የትግሉ ውጤት ፍሬ ማሳየት የጀመረ ፡፡ የመጀመሪው ሙከራ በ 1977 ነበር ፡፡ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ያልነበራችርው እሥራኤልና ኢትዮጵያ መስጢራዊ ስምምነት በመፍጠር ፤ እስራኤል ለኢትዮጵያ መንግስት ወታድራዊ እርዳታ ለመስጠት
ኢትዮጵያ በበኩሏ ቁጥራቸው 200 የሚሆኑ ቤተ እስራኤሎች፤ የቤተ ሰብ ዉህደት በሚል ዉል እስራኤል እንዲመጡ ከስምምነት ደረሱ ፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረት ቁጥራቸው 121 ቤተ እስራኤሎች ለመምጣት ቻሉ፡ ነገር ግህን ይህን ምስጢራዊ ስምምነት በወቅቱ የእስራኤል የዉጭ ጉድይ ሚኒስቴር የነበሩት ሞሸ ዳያን ስላጋለጡት ተቋረጠ፡፡
በ 1979 ዓ/ም የሞሳድ ( የእስራኤል ስለላ ድርጅት) አባላት ስለ ኢትዮጵያ ይሁዲወች ጉዳይ ታጋዮች ከሆኑት መካከል ፈረደ አክሉም፤ ባሩህ ተገኘ፤ ዚምና ብርሃኔ እና ዘካሪያስ ዮና ጋር ሲገናኙ አልያው ሊታደስ ቻለ፡፡ በነዚህ ታጋዮች አማካኝነት አዲስ የአልያ ዕቅድ ተዘጋጀና ፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤሎች ወደ ሱዳን ብዙ ስቃይና እንግልት ያስከተለ የእግር ጉዞ በኋላ እስራኤል ገቡ፡፡
የእግር ጉዞው ሳምንታትና ወራት ያስቆጠረ ነበር ፡፡ በእግር ሲጓዙ ከመንግስት ወታደሮችና ከመንገድ
ቀማኛ ወንበዴዎች መደበቅ ነበረባቸው ፡፡ መንገዱ አስቸጋሪ ከመሆኑ በተጨማሪ የምግብና የውሃ እጥረት ችግሮችም ከባዶች ነበሩ ፡፡ ሱዳን ከደረሱ በኋላም ከስደተኞች መጠለያ ሠፈር ወደ እሥላኤል እስኪመጡ ለብዙ ወራቶችና ብሎም ዓመታት መጠባበቅ ነበረባቸው፡፡ በመጠለያ ሠፈሮችም ጥሩ የጤና አገለግሎትና የንጽህና ጥበቃ ዕርዳታ አልነበረም ፤ የሱዳን መንግስትና ሌሎች ከቦታው የነበሩ ይሁዲ ያልሆኑት ስደተኞችም ከባድ ችግሮችን ፈጠሩባቸው ፡፡ ብዙዎችም ወደ እስራኤል ለመምጣት በተስፋ በመጠባበቅ ወይም በመንገድ ላይ ሳሉ ባጋጠሟቸው ከባድ ችግሮች ምክኒያት ሂዎታቸውን አጡ፡፡ በነዚህ ዓመታት ዉስጥ
ቁጥራቸው 16 ሽህ ቤተ እስራኤሎች እስራኤል ገብተዋል ፡፡ ቁጥራቸው 4000 የሚሆኑት ሀይወታቸውን አጥተዋል ተብሎ ይገመታል ፡፡
ወደ እስራኤል አመጣጡ ሂደት አስር ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን የተከናወነውም በእስራለል ሙሳድ ፤ የቤተ እስራኤሎች አባል የሆኑት ታጋዮች፤ የአየር ሓይልና የባሕር ሃይል ባደርጉት ተብብር ነው ፡፡ አፈጻጸሙም አነስተኛና በዛት ባለው የሰወች ቁጥር ነበር፡፡ በአሜርካ መንግስት አሸማጋይነት ከሱዳን መንግሥታ ጋር ከምስጢራዊ ስምምነት ስለተደረሰ ምጽዐተ ሙሴ ወይም ሚብጻ ሞሼ በሚል ስም በሚታወቀው ( 21 ፡ 11 ፡84
5፡ 1፤፟ 85 ዓ/ም ) ዘምቻ ጊዜ ቁጥራቸው ከ 16 ሽህ በላይ ቤተ እስራኤሎች እሥራኤል መግባት ችለዋል፡፡ ይሁን እንጅ ከአንድ ወር ተኩል በኋላ እሥራኤላውያን ባለስልጣኖች ይህን መስጢራዊ ስምምነት በመገናኛ ብዙሃን ስላጋለጡትና የሱዳንን መንግስትም ስላበሳጨ ቤተ እሥራኤሎች ጨርሰው እሥራኤል ሳይገቡ ተቋረጠ ፡፡ በዚህ ምክኒያት በመላው 80 ኒዎች ዓመት በአነስተኛ ቁጥር ቤተ እስራኤሎች ከሱዳን እስራኤል መምጣታቸው ቀጥሏል፡፡ የቀሩት ቤተ እስራኤሎች በቀጥታ ከኢትዮጵያ እሥራኤል እንዲመጡ በእስራኤል መንግስት ላይ ከባድ የሆነ ግፊት መደረጉ ተቀጠለበት፡፡
ለ 16 ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የእስራኤልና የኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ግንኙነት በ1989 ዓ/ ም እንደገና ሲታደሰ የእራኤል መንግስት ቤተ እስራኤሎችን በቀጥታ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ማምጣት ጀመረ፡፡ ወገኖቻችን ይምጡልን እያሉ የሚታግሉት የቤተ እስራኤሎች አባላትና ይሁዳውያን ድርጅቶች፤ እንደ AAEJ ያሉት ድርጅቶች ቤተ እስራኤሎች መንደራቸውን እየለቀቁ ወደ አዲስ አበባ እንዲያልፉ የሚያበረታታ ጥሪ ስላቀረቡላቸው ቀስ በቀስ እየሄዱ አዲስ አበባ ከሚገኛው የስራኤል ኢምባሲ ጽህፈት ቤት አካባቢ ተሰባሰቡ፡፡ በመጀመሪያ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑት ብቻ እስራኤል ሲመጡ እስራኤል የነበሩትን ቤተ ሰቦችና ወገኖች አላስደሰታቸውም ፡፡ ሰለሆነም የሱዳኑ ጉዞ ሲቋረጥ የቀሩት ቤተ እስራኤሎች መጥተው ከተለዩዋቸው ቤተ ሰባቸው ጋር እንዲዋሃዱ ቅድሚያ ይሰጣቸው
የሚሉ ጥያቄዎች ቀረቡ፡፡ በወቅቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ የርስ በርስ ጦርነቱ አስጊ እየሆነ ስለመጣና የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎች አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ስለተቃረቡ በ1991 ዓ/ም በእስራኤል ኢምባሲ ግቢ ያሉትን ቤተ እስራኤሎች በአስቸኳይ ማውጣት ግዴታ እንደሆነ የእስራኤል መንግስት ከዉሳኔ ላይ ደረሰ ፡፡
ይህን ከባድና ዉስብስብ የሆነ ዉሳኔ ለመተግበር ፤ የእስራኤል ብሔራዊ መ/ ሠራዊት ፤ የእስራኤል ሙሳድ ፤ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ የሶኽኑት ሃይሁዲት ሰዎችና ነባር የኢትዮጵያ ይሁዲወች ተቀናጅተው ግንቦት 23 ቀን 1991 ዓ/ም ሌሊት ሚብጻ ሽሎሞ የሚል ስም የተሰጠው ዘመቻ ተጀመረ ፡፡ በእስራኤል ታሪክ የመጀመሪውና አስደናቂ
የሆነው ይሁዲወችን እስራኤል የማምጣት ዘመቻ ነበር ፡፡ ቁጥራቸው 34 አይሮጵላኖች የተሳተፉበት የአይሮጵላን በረራወች ፤ በ36 ሥዓታት ዉስጥ ቁጥራቸው 14 ሽህ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ይሁዲወች እስራኤል እንዲገቡ ተደርጓል ፡፡
ከሚብጻ ሽሎሞ ከተጠናቀቀ በኋላ የእስራኤል መንገሥት መልዕክተኞችን ወደ ቋራ ላከ ፡፡ በ 80 ዎች ዓ/ም የእትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎች አካባቢዉን ተቆጣጥረውት ሰለነበረ ወደ ቦታው መሄድ ለህይዎት አስፈሪ ነበር ፡፡ በመጨረሻ በ1999 _ 1992 ዓ/ም የቋራ ኗሪ ቤተ እሳራኤሎችም ጠቅለው እስራኤል መግባት ቻሉ፡፡
የመጨረሻወችና አሁንም በመምጣት ላይ ያሉት ፤ ዜራ እሥራኤል ( ፈለስ ሙራ ወይም ሽኤሪት ይሁዴ ኢትዮጵያ ) እየተባሉ የሚጠሩት ናቸዉ ፡፡ ሃረጋቸው ከቤተ እስራኤሎች ሲሆን ከ 19/ኛው ምዕተ ዓመት ጀምረው ወደ ክርስትና ሃይማኖት ሂደዋል ፡፡ ስለሆነም ክርስቲያኖች ሙሉ በሙሉ አልተቀበሏችውም ፤ በዚህ ሁኔታ በሁለቱ ህብረተ ስቦች ተቀባይነት አጥተው የኖሩ ናቸው ፡፡ የትዉልድ ሃረጋችው አባላት ከሆኑት ቤተ እስራኤሎች ጋር መጠነኛ የሆኑ ግንኙነቶች አልተቋረጡም ነበር ፡፡ የእነዚህ ሰወች ወደ እስራኤል መምጣት ሁኔታ አወዛጋቢ ሆኗል፡፡ ወደ እስራኤል መመልስ መብት ያለው ማን ነው የሚለው ሕግ እነሱን አይመለከትም የሚሉ ስላሉ ፡፡ ይሁን እንጅ በርካታወች እስራኤል መጥተው የሚኖሩ ቤተ ሰቦች አሏቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች እስራኤል ከመምጣታቸው በፊት ኢትዮጵያ በመጠባበቅ እያሉ ሃይማኖት የመልወጥ ትምህርት ተሰጥቷቸው ጊዩር ሃይማኖት መቀየር ፈተና ማለፍ አለባቸው ፡፡ ለበርካታ ዓመታትና በተለያየ ጊዜ ከእነዚህ ሰወች መካከል በዙወች እስራኤል መግባት ችለዋል ፡፡ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 50 ሽህ የሚሆኑት እስራኤል ገብተዋል ፡፡ በበዙ ሽህ የሚቆጠሩትም እስራኤል ለመምጣት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ፡፡
እስከ 2020 ዓ/ም መጨረሻ በአጣቃላይ ቁጥራቸው 159 ሽህ 5 መቶ ቤት እስራኤሎች እሥራኤል ዉስጥ የኖራሉ ፡፡ ከዚህ ቁጥር መካከል 88 ሽህ 5 መቶ እትዮጵያ የተወለዱ ሲሆን ፤ 71 ሽህ እስራኤል የተወለዱ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ይሁዳውያን መንፈሳዊ መሪዎች
ከሌላ አገሮች ከሚኖሩት ይሁዲዎች ራባናት ጋር ተመሳሳይ ማዕረግ ያላቸው የቤተ እስራኤሎች ካሃናት ( (ቀሳውስት) ናቸው፡፡በስደት በቆዩባቸው ዘመናት የይሁዲ ሃይማኖት እንዳይጠፋ ምርኩዝና መብራት ሆነው የቆዩት ቀሳውስቱ ናቸው ፡፡ በኦሪት፤ በሃይማኖትና በሕግጋቶች ዕዉቀት ነበራቸው ፡፡ ሃይማኖታዊ ከብረ በዓሎችን ይቀድሱና ይባርኩ ነበር፡፡ በኦሪት መጽሃፍ ጥልቅ የሆነ ዕዉቀት ስለነበራቸው በቤተ እስራኤሎችና በሌሎችም ቃላቸው የተከበረ ነው ፡፡ የሃገር ሽማግሌወች የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅ ካልቻሉ ቀሳውስት የወሰኑት ግን በሁሉም በኩል ተቀባይነት ያገኛል፡፡
የቅስና ትምህርት የሚጀመር በ 7 ወይም በ 8 የዕድሜ ክልል ነው ፡፡ ዲያቆኖች ከመነኮሳት ጋር በአዳሪ ተማሪነት ነበር የሚቆዩ ፡፡ ተማሪው የሃይማኖት ትምህርቱን አጠናቆ ከተፈተነ በኋላ የቅስና ሹመቱን ይቀበላል ፡፡ ሹመት ከመቀበሉ በፊት መዳር አለበት ፡፡ ሹመቱን ከተቀበለ በኋላ ለህብረተ ሰቡ የሃይማኖት መሪ መሆን ይቸላል ብሎ ህብረተ ሰቡ መስማማቱን ማሳዎቅ አለበት ፡፡ ቀሳዉስት የመረጣቸው ሊቀ ካሃናት ተብለው የአካናቢው ቀሳዉስት የበላይ መሪ
ይሆናሉ፡፡ ቄስ ድንግል እሴት ነው ማግባት ያለበት ከሚስቱ ጋርም አይፋታም ልዩ ምክኒያት ካልተፈጠረና ቀሳዉስት ምክኒያቱን መርምረውና አጣርተው ቅስናዉን የማይጎዳ መሆኑን አረጋግጠው ልዩ ፍቃድ ይሰጣሉ ፡፡ የትዳር ባለቤቱ የሞተችበት ወጣት ወይም አዛውንት ቄስ ድንግል ከሆነች እሴት ጋር ብቻ መጋባት ይችላል ፡፡ የሰርጉ ሥነ ሥርዕት በትልቅ ድግስና ዝማሬ ይከናወናል፡፡ ቄስ በቤተ እስራኤሎች ትልቅ ክብር አለው ፡፡ በማንኛውም ነገር የህብረተ ሰቡ አስተዳዳሪወች ናቸው፡፡ የስብዕነት ፤ የንጹህነት፤ የታማኝነትና ፤ የትህትና መለዮወች ናቸው ፡፡ ቄሶች ሁሌም ነጭ ልብስ ነው የሚላበሱ፤ ( የንጹህና የትህትና ምሳሌ )ቀሳውስት ከራሳቸው ባለው የነጭ ሻሽ መጠምጠሚያና በቅዱስ መጽሃፋቸው ይለያሉ ፡፡
ቀሳውስት ሦስት መሠረታዊ ሃላፊነት አላቸው ፡፡ አንደኛው ሃይማኖትን ባስመለከተ ሲሆን ፤ በበዕልና በአዘቦት ቀናት ጸሎት መምራት ነው ፡፡ በበዓላት ጊዜ ቁርባን ማቅረብ፤ እርክስናና ንጽህና ባስመለከተ ፤ ድረሽና ፍች እንዲሁም ኦሪት በማስተማር፤ ፡፡ ሁለተኛው ሥራቸው ፤ ማህበራዊ ጉዳይ ባስመለከተ ነው፡፡ ህብረተ ስቡ አንድነቱን ጠብቆ እንዲኖር ማበረታት፤ አንባጓሮ ሲፈጠር አሸማግሎ ማስታረቅ፤ አመጸኛ በሆኑት ላይ ማዕቀብ ማድረግ ፡፡ ሦስተኛው የቄስ ተግባር፤ እንግዶችን መቀበል ነው ፡፡ ቀሳዉስት እንደ ሌላ ሰወች ብግብርና ሥራ አልነበረም ተግባራቸው ፡፡ በኦሪት ትምህርት ነበር የሚያተኩሩት፤ ኑሮዋቸው በቁጥብ ነበር ከአምራቾች በሚሰጣቸው የሰብል በኩር ይስተዳደሩ ነበር ፡፡ በእያንዳንዱ ትልልቅ ገጠር መንደር ቄስ አለ ይህ ቄስ ፤ ለተልያዩ ሌላ ተንንሽ መንደሮችም የሃይማኖት አገልግሎቶች ይስጣል፡፡
ሌላው ተጨማሪ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚስጡ መነኩሴዎች ናቸው ፡፡ ምንኩስና የተጀመረ በ 15 /ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን ፤ መነኩሴወች ከህብረተ ሰቡ ተለይተው በኦሪት ትምህርት ብቻ ነው ትኩረታቸው፤ እነሱ ናቸው አስተምረው ለቅስና የሚሾሙ፡፡