ወደ እሥራኤል ለመምጣት በመንገድ የህይወት ምስዋዕት የከፈሉት የኢትዮጵያ ይሁዲወች
” የኢትዮጵያ ይሁዲወች በዙ እንግልትና የመከራ ፈተና አለፈው ነው እስራኤል የገቡት ” ፡ በማለት ፡ ቀደም የስራኤል ከኔሴት ( ፓራላማ) አፈ ጉባኤ የነበሩት ሽሎሞ ሂሌል፤ ” ሃሎም ቤን ሶራጊም ” በተባለው ስለ የኤትዮጵያ ይሁዲ ጺዮናውያን እሥረኞች ጉዳይ በሚተርከው መጽሓፍ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ከ1979_ 1990 ዓ/ም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤሎች በሱዳን በኩል እስራኤል ለመምጣት ሞክረዋል፡፡ ብዙወች በእግር ጉዞ ላይ እያሉና ሱዳን ከስደተኞች መጠለያ ስፈር እያሉ ሕይወታቸው አለፈ ፡፡ በእነዚህ ዓመታት ቁጥራቸው 16 ሽህ የሚሆኑት እስራኤል ሲገቡ 4 ሽህ የሚሆኑት ሕያወታቸወን አጥተዋል ተበሎ ይገመታል ፡፡ ( በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው 1620 የሚሆኑት ሙታን እየሩሳሌም ሃር ሄርጽል ከሚባለው ቦታ የሙታን መዘክር ሃዉልት የስም ዝርዝራቸው ይገኛል ፤) እነዚህ ሙታን የእስራኤልን አፈር የመንካት ዕድል ሳያገኙ ነው የቀሩት፤ ስለ እየሩሳሌም ነበር ሲያልሙ የኖሩት ፡ ሕልማቸውን እውን ለማድረግ በመጓዝ ላይ እያሉ ነው ከባድ የሆነውን የህይዎት ምስዋዕት ከፈሉት ፡፡
እየሩሳሌም ለመድረስ ተነስተው በመንገድ ላይና በመጠባበቅ ላይ ሳሉ ሕይወታቸው ያለፈዉ እሴትና ወንድ ጀግኖች ፡ በከፈሉት የሕወት ምስዋዕት፤ ጺዮናዊነት ፤ ሃገር ወዳድነትና ታማኝነት ምን እንደሆነ አስተምረውናል ፡፡
ነብሳቸው ይማር