ስለአልያና የአልያ ሙከራዎች
የኢትዮጵያ ይሁዲወች ከትዉልድ እስከ ትዉልድ ስለ እየሩሳሌም መጓጓትና መናፍቆታቸውን አንድም ቀን አቋርጠውት አታዉቁም ነበር ፡፡ በጸሎትና በዝማሬ ፤ በሥግድ በዓል ፤ በደስታና በሃዘን ጊዜ ፤ እየሩሳሌም ሁሌም ከልባቸው ተለይታ አታዉቅም ነበር ፡፡ በ 1862 ዓ/ም ነበር አባ ምሃሪ የሚባሉ መንፈሳዊ መሪ ቀይ ባሕርን ተሻግረን እየሩሳሌም እንገባለን ብለው ሕዝባቸውን ሲጠሩ ፤ ብዙወች ተከተሏቸው ፡፡ ይሁን እንጅ ሙከራቸው ሳይሳካላቸው ቀረ ፡፡ በርካታ ሰወች በመንገድ ላይ ሳሉ ሞቱ የተረፉት ተመለሱ ፡፡
ይህን የመሰለ አሳዛኝ አዳጋ የደረሰባቸው ቢሆንም ቤተ እስራኤሎች እየሩሳሌም የመመለስ ፍላጎታቸው ጽኑ ነበር ፡፡ ዮሴፍ ሃሌቢ የሚባል ፈረንጅ ይሁዲ በተመሳሳይ ምዕተ ዓመት ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ለቤተ እስራኤሎች ከእየሩሳሌምና በዓለም ከሚገኙት ይሁዲወች ጋር ግንኙነት መፍጠሪያ መስመሮችን ከፈተ፡፡ የዮሴፍ ሃሌቢ ተማሪ የሆነው የዕቆብ ፋይትሎቢች የአስተማሪዉን ፍኖት ተከትሎ ፤ በፕሮፌሶር ታምራት አማኒኤል፤ ጌጤ ኤርሚያስና ዮና ቦጋለ እርዳታ ለቤተ እስራኤሎች ት/ም ቤቶችን
ከፈተ ፡፡ በሌላ ዓልም የሚኖሩት ይሁዲወችም ኢትዮጵያ ውስጥ ይሁዲወች እንደሚኖሩ አስተዋወቀ፡፡ የቤተ እስራኤልን ወጣቶችም ወደ እስራኤልና ኤዉሮፓ በመዉስድ ትምህርት እንዲገበዩ መደረጉ በቤት እሥራኤሎች በኩል የእየሩሳሌም ሕልማቸው ዕዉን ሊሆን ነው የሚለዉን ተስፋ አጠነከረው ፡፡
እስራኣኤል ከተቋቋመች በኋላ የቤተ እስራኤሎችን ጉዳይ አስመልክቶ የእስራኤል መንግሥት የወሰደው አንድም እርምጃ አልነበረም ፡፡ ወደ እስራኤል የመመለስ መብት የሚለው ሕግ ለቤተ እስራኤሎች ከተግባር ላይ እንዲዉል አላሰበበትም ፡፡ እንዳዉም ትክክለኛ ይሁዲነታቸው አጠራጣሪ ነው ማለትም ጀመሩ መንግስታዊና ድርጅታዊ ባለሥልጣኖች ፡፡ የእስራኤል መንግስት ይፋዊ አቋም ይህን የመሰለ ቢሆንም ቁጥራቸው 200 የሚሆኑት ቤተ እስራኢሎች በግላቸው እስራኤል መግባት ችለዋል ፡፡ እንዚህ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑት ሰወች በቆራጥነት ተነሳስትው ለወገኖቻችን እሥራኤል የመምጣት መብት ይሰጣቸው በማለት እስራኤል ዉስጥና በውጭ ሃገራት ስላማዊ ሰልፎች በማካሄድ ጥያቄ አቀረቡ ፡፡ ከተለያዩ ሃገራት መሪዎች ጋር እየተገናኙ ለትግላቸው ትብብር በመጠየቅ ፤ በሰሜን አሜሪካ የተቋቋመው AAEJ የሚባለው ለቤተ እስራኤሎች ጥያቄ ተባባሪ ማህበር ፤ የዩኒበርሲቲ ተማሪወችና ሌሎችም በተቀናጀ ጥረት በእስራኤል መንግስትና በይሁዳውያን ድርጅት መሪወች ላይ ከባድ ተጽዕኖ ፈጠሩ፡፡
በ70 ኛ/ው ዓመት አካባቢ ተግሉ ጥሩ ለውጦችን ማሳየት ጀመረ ፡፡ በምስጢራዊ ዘዴወች የሁዲዎችን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል መዉሰድ ተጀመረ ፡፡ ከሚብጻ ሞሸና ሚብጻ ሽሎሞ ሌላ የተለያዩ መስጢራዊ እርምጃወች ተከናዉነዋል ፡፡ የኢትዮጵያ ይሁዲወች ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል መምጣት አሁንም እንደቀጠለ ነው ፡፡
ቤተ እስራኤሎች በሱዳን በኩል ወደ እስራኤል መምጣት (ሚብጻ አሒም)
(1979-1990)ከ 1979 – 1990 ዓ/ም በበዙ ሽህ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤሎች በሱዳን በኩል እስራኤል ገብተዋል ፡፡ ቤተ እስራኤሎችን በሱዳን በኩል ወደ እስራኤል ማምጣት የተቻለ ፤ የእስራኤል ሞሳድ መልዕክተኞችና ሱድስን የነበሩት ቤተ እርስራኤሎች ፤ እንደ ፈረደ አክሉም፤ ባሩህ ተገኘ ፤ ዚምና ብርሃኔ እና ዘካሪያስ ዮና የመሳሰሉት ትብብር በማደረግ ፤ ሱዳን የነበሩት ቤተ እስራኤሎች ወደ እስራኤል
እንዲመጡ ለማደርግ ሁኔታወችን ስላመቻቹ ለሁዲወች ወደ እስራኤል የመምጣት አጋጣሚወች ተፈጠሩ ፡፡ ቤተ እሥራኤሎች
ከሀገር ቤት ወደ ሱዳን በጉዞ ሳሉና ሱዳን ዉስጥ እያሉ ከባድ የአካልና የህሌና ስቃዮች እንዲሁም የሞት አደጋወች ደርሰውባቸዋል ፡፡ ቤተ እስራኤሎች ከቤታቸው እየወጡ ወደ ሱዳን በመጓዝ ላይ ሳሉ ትልቅ ችግር የሆነባቸው የመንግስት ባለ ሥልታኖች ይዘው እንዳያስሯቸው እንዴት አድርገው በምስጢር ከቤታቸው መዉጣት እንድሚችሉ ነበር፡፡ ለጉዞ መዘጋጀቱ ፤ ጉዞ መጀመሩ ሁሉም ነገር በምስጢር ነበር ፡፡ በሌሎች በኩል ጥርጣሬ ላለመፍጠር ፤ ቤተ ሰብ በአንድ ላይ ሳይሆን ተከፋፍለው ወደ ሱዳን መንገድ እንዲጀምሩ ነበር የቤተ ሰብ ዕቅድ ፤ በተለያየ ዕድሜ ክለሎች የሚገኙ እሴቶች ወንዶች አዛውንቶችና ታዳጊ ልጆች ናቸው ለጉዞ የወጡት፡፡ ነብሰ ጡር የነበሩት እሴቶችም ያለ ፍርሃት ለጉዞ ተነስተው በመንገድ እያሉም ወልደዋል ፡፡የእግሩ ጉዞ ሣምንታትና ወራት ያስቆጠረ ነበር ፡፡ በሌሊት ሲጓዙ አድረው ቀን ተደብቀው ይዉላሉ በመንግሥት ወታደሮች እዳይያዙና ሽፍቶችንም በመፍራት ፡፡ በበጋ ወራት ሙቀቱ ከባድ ስለሚሆን በሌሊት መሄድ ይመርጡ ነበር ፡፡ በአንዳድ ቦታወች በቀንም ሂደዋል፤ መንገዱ ጉራንጉርና ዉጣ ውረድ የበዛበት፤ በጥቅጥቅ ጫካ የተሸፈነ ፤ ከባድ የሆነ ፈሳሽ ወንዞች የሌሉበት እንዲሁም በርሃ ምድረ በዳ ያለበት፤ ከአደገኛ አራዊቶችና መርዘኛ እባቦች ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ግዴታ ነበር ፡፡ ሌላው ተጨማሪ ችግር የተሸከሙት ምግብና ውሃ አነስተኛ ስለሆነ ብዙ ከተጓዙ በኋላ በተለይ ከምድረ በዳ ሲድርሱ ከባድ ችግሮች አጋጠሟቸው ፡፡ ራሃቡ የውሃ ጥማቱ ፤ የጽሃይ ሀሩሩ አደከማቸው ፡፡ ስለ እየሩሳሌም ጓጉተው ከቤታቸው ወጥተው ህልማቸውን እዉን ሳያደርጉ በመገድ የሞቱትን በፍጥነት ከመንገድ አጠገብ እየቀበሩ የተርፉት ግን ጉዟቸውን ሳያቋርጡ ቀጠሉበት ፡፡
ሱዳን ሲደርሱ የቀይ መስቀል ማኅበር ታቋቋማቸው መጠለያ ድንኳኖች እንዲገቡ ተደረገ ፡፡ የሚበላና የሚጠጣ ውሃ በቀላሉ አልተገኘም ፤ ሙቀቱ ፤ የሰው ብዛትና መጨናነቁ ፤ የቦታው መቋሸሽ ፤ ከባድ በሽታ አደረሰባቸው ፡፡ የሚሞተው ሰው ቁጥርም እየበዛ ሄደ ፡፡ በተለይ ታዳጊ ልጆችና ህጻናት በበዛት ሞቱ ፡፡ ዘረፋና እሴቶችን በጉልበት መድፈር የወንበዴወች የዘወትር ተግባር ሆነ ፡፡ ይህ አልበቃቸው በሎ ለሌላ አዳጋም ሊጋለጡ ሆነ ፤ ይሁዲወች መሆናቸውን ያወቁት ሱዳኖችና ሌልም ስደተኞች ጉዳት ማድረስ ጀመሩ፡፡ አዳጋውን በመፍራት ይሁዲዎች በስዉር ሃይማኖታቸውን ከመጠበቅ አልተቆጠቡም ፡፡ በመንገድ ላይ ሳሉ ያሳለፉት ሥቃይና መከራ ሳይበቃቸው ሌላ ከባድ ፈተናዎች በየጊዜው አጋጠሟቸው፡፡ ይህ ስቃይና መከራ አብቅቶ መቸ እሥራኤል እንደሚገቡ አለማወቃቸው አንዱ ችግር ነበር ፡፡ እንደሚታወቀው ከስደተኞች ሠፈር ከወራት እስከ ዓመታት የቆዩም አሉ ፡፡
ቤተ እሥራኤሎች ከስደተኞች ሠፈር ሳሉ ኮሚቴ በሚል ስም ይጠራ የነበረው አካል አባላት ከእስራኤል ሞሳድ ጋር በመተባበር ይሁዲወች የት እንዳሉ እየፈለጉ ፤ ገንዘብና፤ መደሃኒት መስጠት ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወር የሚያስችል የይለፍ ፍቃድ ማዘጋጀት ፤ ከዚያም በምስጢር ወደ እስራኤል ለመውሰድ ከሄዱት የሞሳድ ሰወች ጋር ካሉበት ቦታ ወስዶ ማገናኘት ነበር ተግባራቸው ፡፡ ህይወታቸውን ለአዳጋ በማጋለጥ ነበር የሠሩት ፡፡ አንዳንዶችም በሱዳኖች ተይዘው በጺዮናዊነት ሥራቸው ተወንጅለው ብዙ ሥቃዮች ደርሰውባቸዋል ፡፡ ይሁን እንጅ በሌላ በኩል
የኮሚቴው አባላት የተጣለባቸውን ዕምነት በማጉደል መብታቸውን ለመጥፎ ነገር ተጠቅመው በወገናቸው በተለይ በሴቶች ላይ በደል አድርሰዋል የሚሉ ወቀሳወች ተሰንዝረውባቸዋል ፡፡ ስለሆነም ይህን የመሰለ ዋቀሳ የሚያቀርቡት ሰዎች ቁጥር አነስተኛ ነው ይባላል ፡፡ አብዛኛዎች በጀብዱነትና በድፍረት ህይወታቸውን ለአዳጋ በማጋለጥ ነው የሠሩ የራሳቸውን ወደ እስራኢል የመምጣት ዕድል እያሳለፉ ነበር የሠሩት ፡፡ አንዳንዶች እስራኤል ከመጡ በኋላም ወደ እትዮጵያና ሱዳን ተመልሰው ይሁዲወችን ወደ እስራኤል ለማምጣት ተባብረዋል ፡፡
ይሁዲወች ከሱዳን ወደ እስራኤል የመጡት የሞሳድ ሰዎች በምስጢር ባዘጋጇችው የተለያየ መንገዶች ነው ፡፡ አንደኛው/ ፤ ሱዳን ያሉትን ስደተኞች ለመቀበል ፍቃደኛ የሆነ አገር የተገኘ አስመስለው የተጭበረበረ የፍቃድ ወረቀት አዘጋጅተው ከሱዳን ወደ ሌላ አገር ከሚበር አይሮፕላን እያሳፈሩ መላክ ፡፡ ቤት እሥራኤሎችን ያሳፈራቸው አይሮፕላን ከአንድ አገር ሲያርፍ ወዲያውኑ ከሌላ አይሮፕላን አሳፍሮ እሥራኤል ማምጣት ነበር ፡፡
ሁለተኛው/ ዘዴ ፤ ከስደተኞች ሠፈር ያሉትን ይሁዲወች ወደ ፖርት ሱዳን ወደብ አጓጉዞ ከዚያ የእስራኤል ባሕር ኅይል ኮማንዶ ወታደሮች በመርከብ አሣፍረው ወደ እስራኤል በማምጣት ነበር ፡፡ የሞሳድ ሰወች በሱዳን ወደብ ይሁዲወችን ለማምጣት በተጭበረበረ ዘዴ ነበር የተጠቀሙት ፡፡ ከወደቡ አጠገብ የሃገር ጎብኝወች መዘናኛ ቦታ ማደራጀት እንፈልጋለን በሚል ሰበብ ከሱዳን መንግሥት ፍቃድ ጠይቀው ሰለተፈቀደላቸው፤ ለአገር ጎብኝወች መዝናኛ በተለይ ከባሕር ጠልቀው መዋኘት ለሚወዱ ስወች ቦታዉን በጥሩ ሁኔታ አዘጋጁ ፡፡ ከዛ ሆነው ባወጡት ዕቅድ መሠረት ይሁዲወችን በመርከብ እስራኤል አመጧቸው ፡፡
ሦስተኛው / መንገድ ፤ ከስደተኞች ሠፈር የነበሩትን ይሁዲወች በምስጢር አውጥቶ ሱዳን ውስጥ ራቅ ካለ በርሃ ምድረ በዳ በልዩ ሁኔታ ከተዘጋጀ ጊዜያዊ አይርፕላን ማረፊያ አደርሶ ማሳፈርና እስራኤል ማምጣት ነበር ፡፡
በዚህ ሁኔታ( ሚብጻ ሞሸን ጨምሮ ) ቁጥራቸው 16 ሽህ የሚሆኑ ቤተ እሥራኤልች እስራኤል ገብተዋል ፡፡
ሚብጻ ሞሸ እና ሚብጻ ሽባ
(21.11.1984-05.01.1985)ስለሚብጻ ሞሼና ቤተ እስራኤሎች በሱዳን በኩል እሥራኤል ለመምጣት ያላሳለፉትን መከራ ባስመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ለማግኘት ( በሊንኩ ተጠቀሙ )
በ 1984 ዓ/ም ከኤትዮጵያ ሱዳን የሚገቡት ይሁዲወች ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ የጤናቸው ሁኔታ አስከፊ እየሆነ መጣ ፡፡ የሚሞቱት ሰወች ቁጥርም በየቀኑ እየጨመረ ስለሄደ በአነስተኛ ቁጥር ሲካሄድ የቆየው ሰወችን ወደ እስራኤል የማማጣት ሥራ ተቀይሮ ሌላ እርምጃ መወሰድ
እንዳለበት የእስራኤል መንግሥት ከውሳኔ ላይ ደረሰ ፡፡ በአሜሪካ መንግሥት ጣልቃ ገብነትና አሸማጋይነት ከሱዳን መንግሥት ጋር ከምስጢራዊ ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ የሱዳን መንግሥት ገንዘብ ተቀብሎ ይሁዲወች ከሃገሩ እንዲወጡ ሊፈቅድ ተስማሙ ፡፡ ስምምነቱም ምስጢሩ ሳይጋለጥ ይሁዲወች ከሱዳን በቀጥታ ወደ እስራኤል ሳይሆን በሌላ አገር በኩል አድርግው ይሂዱ የሚል ነበር፡፡
ሚብጻ ሽሎሞ ህዳር 21 ቀን 1984 ዓ/ ም ነው የተጅመረ ፡፡ አንደ ጆርጅ ጉተልማን የሚባል የቤልጅክ ዜግጋ የሆነ ይሁዲ የራሱ የሆነ አየር መንገድ ካምፓኒ ስለነበረው አዉሮፕላኖቹ ቤተ እስራኤሎችን ከሱዳን እያሳፈሩ እንዲያወጡ ስለፈቀደ በሳምንታት ዉስጥ በብዙ ሽህ የማቆጠሩ ቤተ እስራኤሎች ከሱዳን ወጥተው እስራኤል መግባት ቻሉ ፡፡ ይሁን እንጅ የእስራኤል ባለሥልጣኖች መስጢሩን ይፋ ስላደረጉት ሁሉም ጠቅለው እሥራኤል ሳይገቡ ተቋረጠ ፡፡ የምስጢሩ መጋለጥ የሱዳንን መንግሥት ስላስቆጣ ይሁዲወች ከሱዳን እንዳወጡ ከለከለ፡፡
ሚብጻ ሞሸ በተካሄደባቸው ቀናት ቁጥራቸው 6 ሽህ 364 ይሁዲወች እስራኤል ገብተዋል ፡፡ ሱዳን የቀሩትን ይሁዲወች ለማውጣት የአሜርካ መንግሥት ከሱዳን መንግሥት ጋር እንደገና በምስጢር ከሌላ ስምምነት ላይ ስለተደረሰ ሱዳን ዉስጥ ከስደተኞች ሠፈር የቀሩት ቤተ እስራኤሎች በአሜሪካ አየር መንገድ አይሮፕላኖች ተሳፍርው እንዲወጡ ተደረገ ፡፡ ” ሚብጻ ሽባ ” በሚል ስም ተሰይሞ መጋቢት 22 ቀን 1985 ዓ/ም በአሜሪካ መከላከያ ሠራዊት እይሮፕላኖች ቁጥራችው 494 ሰዎች እሥራኤል ገቡ ፡፡ ሌላ ቁጥራቸው 100 የሚሆኑትም በሌላ አይሮፕላን ተሳፍረው እስራኤል መግባት ችለዋል ፡፡
” በሚብጻ ሞሸና” በ “ሚብጻ ሽባ” ቀጥራቸው 7 ሽህ ቤተ እስራኤሎች እሥራኤል ገብዋል ፡፡
ሚብጻ ሽሎሞ
(23.05.1991-25.05.1991)እስራኤልና እትዮጵያ ለ 16 ዓመታት ተቋርጦ ተቆየውን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት በ1989 ዓ/ም እንደገና ማደሳቸውን ይፋ አደርጉ ፡፡ ይህ አዲስ ሁኔታ ይሁዲወች በቀጥታ እስራኤል የመምጣት ዕድል ማግኘት አስቻለ ፡፡ አዲስ መሥመር መከፈቱ ለኢትዮጵያ ይሁዲወች ትልቅ ተስፋ ሆነ ፡፡ በተለያዩ ድርጅቶች በተለይ AAEJ አበረታችነትና እርዳታ ቤተ እስራኤሎች ከመኖሪያ ቤታቸው እየወጡ ወደ አዲስ አበባ ሂደው ከእስራኤል እምባሲ አካባቢ ሠፈሩ ፡፡ ወደ እሥራኤል ለመምጣት አዲስ አበባ እያሉ የተለዩ ዕርዳታወች፤ እንደ ሕክምና፤ ትምህርትና ሌላ አስፈላጊ የሆኑ እርዳታውች ተሰጣቸው፡፡ ለቤተ እስራኤሎች ልዩ
ግቢ ተዘጋጅቶ በሃላፊነት AAEJ ; ጆይንት ፤ ሶክኑት ሃይሁዲት፤ NACOEJ እና አልማያ ፤ ሃላፊወች ሆነው ማስተዳደር ጀመሩ ፡፡
በመጀመሪዎች ዓመታት ወደ እስራኤል የመጡት ሰወች ቁጥር አናስተኛ ነበር ፡፡ እስራኤል ለመምጣት ከሚጠባበቁት 20 ሽህ ሰዎች መካከል ፤ ከ1990 እስከ 1991 ዓ/ም ቁጠራቸው 7 ሽህ ብቻ ናቸው እሥራኤል መግባት የቻሉት ፡፡ የሱዳኑ መንገድ በመቋረጡ መክኒያት ከቤተ ሰብ ጋር የተለያዩት ሰወች እስራኤል መጥተው እንዲቀላቀሉ የቅድሚያ ዕድል የሰጣቸው በማለት በመግሥት ላይ ከባድ ግፊት ማድረግ ተጀመረ ፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሲካሄድ የቆየው የርስ በርስ ጦርነት እየከፋ በመሄዱ ምክኒያት ይሁዲወች በተቀላጠፈ ሁኔት ወደ እስራኤል ይምጡ የሚለው ግፊት ጠነከረ ፡፡ የእስራኤል መንግስትም ሁኔታው አስጊ መሆኑን በመገንዘብ ሚያዚያ ወር 1991 ዓ/ም ሁሉንም ጠቅሎ ለማምጣት ከዉሳኔ ላይ ደረሰ ፡፡ ይሁን እንጅ በጊዜው የኢትዮጵያ መሪ የነበረው መንግስቱ ኅይለ ማሪያም ችግሮች መፍጠር ጀመረ ፡፡ ከሥልጣኔ ለማውረድ እየተዋጉኝ ያሉትን ጠላቶች እንዳሸንፍ አሜሪካና እስራኤል የገንዘብ እንርዳታ ይስጡኝ አለ ፡፡ 35 ሚኒዮን የአሜሪካ ዶላር እንሰጥሃለን ሲባል ይሁዲወች ከኢትዮጵያ ወጥተው እስራኤል እንዲሄዱ ፈቃድ ሰጠ ፡፡ የመንግስቱ ኅይለ ማሪያም ሥልጣን ተቀናቃኞች አዲስ አበባ ለመግባት ሲቃረቡ ይሁዲወች ጠቅለው እስኪወጡ ለተወስኑ ቀናት እንዲታገሱ አሜሪካ መንግስት ጥያቄ ስላቀረበ እነሱም ታግሰው ዕድሉን ሰጡ ፡፡
ሚብጻ ሽሎሞ የሚል ልዩ ስም ተሰጥቶት ፤ የእሥራኤል መ/ ሠራዊት ፤የሞሳድ ፤የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ሃሶክኑት ሃይሁዲትና ቀደም ከኢትዮጵያ የመጡት ቤተ እስራኤሎች በመተባበር ይሁዲወችን ከእትዮጵያ የማምጥት ዘመቻ ተጀመረ ፡፡ ግንቦት 23 ቀን 1991 ዓ/ም ሌሊት ሚብጻ ሽሎሞ ተጀመረ ፡፡ አዲስ አበባ የነበሩት ቁጥራቸው 120 የሚሆኑ ሠራተኞች እስራኤል ለመምጣት ሲጠባበቁ የነበሩትን ይሁድወች ከያሉበት እየጠሩ ከእምባሲው ግቢ አጠገብ እንዲሰበሰቡ ካደርጉ በኋላ በአውቶቡስ እያሳፈሩ ወደ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያው ወሰዷቸው ፡፡ በበነጋታው 34 የእስራኤል አውሮጵላኖች ይሁዲወችን እያሳፈሩ በተከታታይ ወደ እስራኤል ተጓዙ ፡፡ አውሮፕላኖች ማሳፈር ከሚገባቸው የሰው ቁጥር በላይ ይዘው ነበር ወድ እስራኤል የበረሩት ፡፡ አንዱ አይሮፕላን በዓለም የጀኒስ ሪኮርድ ሰብሮ ( 1088 ሰወችን) አሳፍሮ እስራኤል ገብቷል ፡፡ ሚብጻ ሽሎሞ ግንቦት 25 ጥዋት ላይ ተጠናቀቀ ፡፡
ሚብጻ ሽሎሞ ይሁዲወችን ከኤትዮጵያ እስራኤል የማምጣት ዘመቻ በታሪክ የመጀመሪያ ሆኗል፤
በ 36 ሣዓታት ውስጥ ቁጥራቸው 14 ሽህ ይሁዲዎች ከኤዮጵያ እስራኤል ገበተዋል ፡፡
ስለቋራ ይሁዲዎች አመጣጥ
(1992-1999)እስከ 90 ናዎች ምዕተ ዓመት በቋራ የነበሩት ይሁዲወች እስራኤል አለመጡም ፡፡ የመንግስት ተቃዋሚወች አካባቢውን ስለተቆጣጠሩት ይሁዲወች በቀላሉ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ አልቻሉም፤፡፡ በ 1991 ዓ/ም በኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርንርቱ ሲያባቃ መንገዱ ክፍት ሆነ ፡፡ የሶክኑት ሃይሁዲትና የጆይንት ሠራተኞች ወደ ቋራ ሂደው እስራኤል የመምጣት መብት ያላቸውን ማጣራት ጀመሩ፡፡ በዙ ጊዜ ነበር የወሰደ የማጣራቱ ሂደት፡፡ ቀደም ብለው እስራኤል የመጡት የቋራ ይሂዲወች ቤተ ሰቦች በእስራኤል መንገሥት ላይ ከባድ ተጽዕኖ ስላደርጉ በ 1998 ዓ/ም ዉሳኔ ተላለፈ ፡፡ ውሳኒውም አስፈላጊው የማጣራት ሂደት ተቀላጥፎ የቋራ
ቤተ እሥራኤሎች ይምጡ የሚል ነበር ፡፡ በዚህ ውሳኔ መሠረት በቀጣዩ ዓመት አብዛኞች የቋራ ይሁዲወች እስራኤል ግቡ፡፡
ቁጥራቸው 5 ሽህ የሚሆኑት የቋራ ቤተ እስራኤሎች ናችው እሥራኤል የገቡት ፡፡ ባጠቃላይ አምስት ሽህ ይሁዲዎች ከቋራ እሥራኤል ገብተውል ፡፡
የቤተ እስራኤል ዝርያ ያላቸው እስራሌል መምጣት
(1992-2022)የነዚህ ሰወች መነሻ ከእትዮጵያ ይሁዲዎች ሲሆን ከ19/ ኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ ሀይማኖታቸውን ወደ ከርስትና የለወጡ ናቸው ፡፡ ኑሯቸው ተክርስቲያኖች ጋር ሙሉ በሙሉ የተቀላቀለ ሳይሆን በይሁዲወችና በክርስቲያኖች መካከል ነው፡፡ይሁን እንጅ ከቤተ እሥራኤል ዘመዶቻቸው ጋር ግንኙነታችውን ያላቋረጡም ነበሩ ፡፡
ሚብጻ ሞሸ በተካሄደበት ጊዜ ቁጥራቸው 2 ሽህ የሚሆኑ የዜራ እስራኤል አባላት አዲስ አበባ ነበሩ ፡፡ ይሁን እንጅ ወደ እስራኤል መግባት የሚያስችለው ሆክ ሃሽቡት የሚባለው ሕግ እነሱን የሚያካትት ስላልሆነ አይመጡም ተባለ ፡፡ አዲስ አበባ ሁነው እስራኤል የመምጣት መብት ይሰጠን በሚል ጥያቄ ትግላቸውን ቀጠሉ ሌሎችም ካገር ቤት እየመጡ ተጨመሯቸው፡፡ ስሜን አሜሪካ የሚገኘው NACOEJ የሚባል ድርጅት እየረዳቸው ሲታገሉ ቆይተው በርካታወች እስራኤል መግባት ችለዋል ፡፡
በ1992 ዓ/ም በጊዜው የክሊታ ( የዲስ ገቢወች ጉድይ) ሚኒቴር የነበሩት ያኢር ጻባን ባስተላለፉት ውሳኔ የመጀመሪያ ደረጃ ቤተ ሰብ ያላቸው የዜራ እስራኤል አባላት የቤተ ሰብ ውህደት በሚል ምክኒያት የመጣት ዕድል ተሰጣቸው፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ውሳኔ ተቀይሮ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙት ሁሉ (4000) የሚሁኑት እስራኤል የመምጣት ዕድል ተሰጥቷቸው ሃይማኖታቸውን ወደ ይሁዲነት ይቀይሩ የሚሉ ተጽዕኖች ስለተፈጠሩ በዚህ ሁኔታ በተለያዩ ጊዚያቶች በብዛት እስራኤል ለመግባት ችለዋል ፡፡ ዛሬም ቁጥራችው በርካታ የዜራ ቤተ እሥራኤል አባላት እስራኤል ለመምጣት በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ መጋቢት ወር ላይ 2021 ዓ/ም ( ጹር እስራኤል ) የሚል ስም በተስጠው የማምጣት ዘመቻ በዙወች እስራኤል ገብተዋል ፡፡
የዜራ እስራኤል አባላት እስከ ዛሬ ቁጥራቸው 50 ሽህ የሚሆኑት እስራኤል ገብተዋል ፡፡