ቤተ እስራኤሎች ተሰደው ኢትዮጵያ ከሂውዱበት ቀን ጀምሮ ወደ እስራኤል ለመመልስ ጉጉታቻቸው አንድም ቀን አልተቋረጠም ፡፡ የዕለት ተዕለት ሥራቸው እየሩሳሌምን አዘውትርው ማውሳት ነበር ፡፡ በጸሎትና ፤ በሃዘን ጊዜም ፤ ብዙ ችግርና ስቃይ ቢያጋጥማችውም ሃይማኖታቸውን ተጠንቅቀው ነበር ጠብቀው የኖንሩት ወደ
እየሩሳሌም የመመለስ ምኞታቸውና ጉጉታችው አንድም ቀን አልተቋረጠም ፡፡ የመጀመሪው ወደ እስራኤል የመምጣት ሙከራ የተደረገ በ 19/ነኛው ምዕተ ዓመት ነበር ፡፡ በዚህ ዓመት አጋማሽ ላይ (1855) ዳኒኤል ቤን ሃናኒያ ሞሸ ከሚባለው ልጁ ጋር ሆኖ በጺዮናዊነት ስሜት ተነሳስተው እየሩሳኤም መጡ ፡፡ ሌላው ታሪካዊ ወደ እየሩሳሌም የመምጣት ሙከራ የተደረገ በ 1862 ዓ/ም ነበር ፡፡ አባ ምሃሪ የሚባሉት መንፈሳዊ መሪ ሕዝባቸውን ወደ እየሩሳሌም እንሂድ ብለው በማነሳሳት የእግር መንገድ ጀመሩ ፡፡ ይሁን እንጅ ሙከራው ስለከሸፈባቸው የብዙ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በኢትዮጵያ ይሁዲወችና በሌላ ሃገራት በሚኖሩት ይሁዲወች መካከል ግንኙነት የተፈጠረ ፤ ዮሴፍ ሃሌቢ የሚባል የሴም ቋንቋ ተመራማሪ ኢትዮጵያ ሂሄዶ ሲያገኛቸው ነበር ፡፡ ቀጥሎም የሱ ተማሪ የነበርው ያዕቆብ ፋይትሎቢች ነበር ግንኙነቱ እንዲጣናከር ጥረት ያደረገ ፡፡ የግኙነቱ መታደስ ወደ እየሩሳሌም የምንመለስበት ጊዜ ተቃረበ የሚል ተስፋ በቤተ እስራኤሎች ልብ ማሳደር ቻለ ፡፡ ስለሆነም ስለሃይማኖት ጉዳይ ወሳኞች የሆኑት ራባናትና የመንግሥት ባለሥልጣናት ቤተ እስራኤሎች እዉነተኛ ይሁዲወች ስለመሆናቸው ተጠራጣሬ አደርባችው ፡፡ ይሁን እንጅ በ 1955ዓ/ም በእስራኤል ሀገር ትምህርት እንዲማሩ እሴትና ወንድ ወጣቶች ከኢትዮጵያ እስራኤል እንዲመጡ ተደረገ ፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ከፊሎች ወደ እትዮጵያ ተመለሰው የ" ኦርት" ድርጅት ታቋቋመው ትምህርት ቤት አስተማሪወች ሆኑ ፡፡
በ 1973 ዓ/ም የስራኤል ሊቀ ራባናት የነበሩት ራብይ ኢባዲያ ዮሴፍ በጻፉት ሃይማኖታዊ ውሳኔ ፤ ቤተ እስራኤሎች " ፈላሾች " እዉነተኛ ይሂዲወች ናቸው አሉ ፡፡ ይህ ዉሳኔ በእስራኤል መንግሥት በኩል ተቀባይነት አግኝቶ ሃምሌ 25 ቀን 1975 ዓ/ም ቤት እስራኤሎች እንደማንኛዉም ይሁዲ እስራኤል የመምጣት መብት አላቸው ተብሎ በይፋ ተወሰነ ፡፡ በ 1977 ዓ/ም ምናሄም ቤጊን የእስራኤል ጠ/ ሚኒስትር ሁነው ሲመረጡ የኢትዮጵያን ሁድወች አምጡልኝ ብለው ለሞሳድ( የእሥራኤል መረጃ ደርጅት ) ሰራተኞች ትዕዛዝ ሰጡ ፡፡ በትምህርት ቤት መምህር የነበረው ፈረደ አክሉም የኢትዮጵያ መንግሥት ይዞ እንዳያስረው ስለፈራ ከኢትዮጵያ አምልጦ ሱዳን ስለገባ ሱዳን ሁኖ እስራኤል ለነበርው ሃይም ሃላህሚ ለተባለ የሙሳድ አባል ደብዳቤ ላከ ፡፡ ይህ ሁኔታ ነበር የሱዳን ጉዞ እንዲጀመር በሩን ከፍቶ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤሎች ሱዳን ገብተው ከስደትኞች ሠፈር ሳሉ በምስጢርዊ ዘዴወች እሥራኤል እንዲመጡ የሆነ ፡፡
ወጣቶች ፤ አዛውንቶች ሙሉ ቤተ ሰብ ናቸው ከቅድስት እየሩሳሌም የመድረስ ሕልማቸውን እዉን ለማድረግ ወደ ሱዳን የተጓዙት፡፡ ጉዞው እጅግ የከፋ ነበር፤ በሽፍቶች በመዘረፍ ፤ እሴቶ በጉልበት በመደፈር ፤ በሞት፤ ገና እትዮጵያ ምድር እያሉም ሆነ ሱዳን ከስደተኞች መጠለያ ቦታ እያሉም ፡፡
በ 1991 ዓ/ም እስራኤል የመጣች እሴትዮ ከተናገረችው ፤ በመንገድ ሳለች ልጇ ሞተችባት ፤ የአባቷ መዳረሻ የት እንድሆነ እስካሁን አታውቅም ፡፡
በመንገድ ላይ እያለን መንገድ መሪወች ጣጥለውን ጠፉ ፤ ለሦስት ወደ ሱዳን ጉዞ የጀመርነ በ 1989 ነበር፤"
ወራት ያለ ምግብና ውሃ በማጣት ተሰቃየን ፤ በርሃብ እንዳንሞት አፈሩን በላን ፤ በዚህ እጅግ አስከፊ የሆነ መንገድ ላይ እያለን አንድ ሰው የሌለበት የሱዳኖች ጦር ሠፈር ደረስነ ፤ እንደ አጋጣሚ ከቦታው አንድም ሰው ስላልነበረም ለምግብ የሚሆን ዲቄት አግኝተን ለ 30 ሰወች ተከፋፍለን ልጆች በራህብ እንዳይሞቱ ቅንጨ ( ዳይሳ ) እየሠራን አበላናቸው ፡፡ ለጀን ግን ከሞት ላተርፋት አልቻልኩም ፤ ሞተች ፤ ከመንገድ ጥያት ሄድኩ አባቴም ሰለደከመው ትንሽ ለረፍ በሎ እንደተቀመጠ በዚያው ቀረ፤ ልጀን ቀበርኳት ፡፡ እስካሁን እንዳመመኝ የሚኖር ያባቴ መዳረሻ ነው ፡፡ ሌሎች ቤተ ሰቦቸ እስራኤል ሲመጡ ስላባቴ ስጠይቃቸውም መለስ መስጠት አይፈልጉም ፡፡ ከእኔ የሚደብቁት ነገር ያለ ይመስሉኛል ፡፡ አባቴ ምን እንደሆነ ማወቅ ስለምፈልግ እባካችሁ እርዱኝ ፡፡ የአዕምሮ ህመምተኛ ሁኛለሁ ፤ የምኖረው ሁሌ በጭንቀት ስለሆነ በአዕሮ ዶክተሮች ፤ሳይኮሎጂስትና ሣይካትሪክ ዕርዳታ ላይ ነው እምኖር "
ሱዳን በስደተኞች ሳሉ የእትዮጵያ ይሁዲወች ከባድ ችግሮች ደርሰውባቸዋል፤ ተልቁ ፍርሃት ይሁዲዎች መሆናቸው እንዳይታወቅ ነበር፤ ሌላው ደሞ በሽታው፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ሰወች ህይወት አለፈ፡፡ ኑሮው አስከፊ ነበር፤ ወንበዴዎች በብዛት በየቦታው ነበሩ ፡፡
እናቷና የስድስት ዓመት ልጇ የሞቱባት እሴትዮ ከተናገረችው ፡፡
እሥራኤል አገር እንግባ ብለን እኔ ባለቤቴና አራት ልጆች ( የ 41 ዓመት እሴት ልጅ ፤የ 11 ዓምት ወንድ ልጅ ፤የ 8 ዓመት ወንድ ልጅ እና የ 6 ዓመት እሴት ልጅ ) እናቴም ትልቅ እህቴ እሴት ልጇ ፤ እንዲሁም ትንሽ እህቴ ሁነን እየሩሳሌም ለንገባ ነው በሚል ተስፋ በጥዋቱ ከቤታችን ወጥተን መንገድ ጅመርን፡፡ ለሦስት ወራት ነበር የተጓዝነ ፤ ፡፡ በሌሊት ሳንተኛ አድረን ቀን ሲሆን እንሄዳለን፤ ፡፡ መንገዱ ከባድ ነበር ርሃቡ ውሃ ጥማቱ ፤ ምግብና ዉሃ አቋርጦ አለቀብን፤ መንም ነገር የለነም ፤ በዚህ ችግር ምክኒያት ሁለቱን እህቶቸን አጣሁ፤ሞቱ
፤ እኔም ነፍሰ ጡር ነበርኩ ፤ ሱዳን ስንገባ ከባድ ችግር ደረሰብኝ፤ ሁሉም ነገር ከባድ ነበር ፤ ሱዳን እያለሁ ወንድ ልጅ ተወለደ ፡፡ ሲወለድ የህወት ምልክት ስላልታየበት ሞቷል ብለን ነበር ያሰብነ፤ ይሁን እንጅ እግዚአብሔር ነብስ ዘርቶለት በህይወት መኖሩን አረጋገጥን፤ በችግሩ ምክኒያት የማጠባበት ጡቴ ደርቀ፤ ወተት የለዉም፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ አንድ ዓመት ሱዳን ስንቆይ እናቴ ሱፍ ዉሃ ከሚባለው ቦታ ሞተችብኝ ፤ የሥድስት ዓመት ልጀ ገዳሪፍ ከሚባለው የስደተኞች ሰፈር ሞተች ፡፡ አንድ ዓመት ሱዳን ቆይተን የእስራኤል አይሮፕላን ወሰደን "
ይህን ታሪክ ያገኘነው ጥቅምት 2015 ዓ/ም " እስራኤል ለመግባት በመንገድ ሳሉ ላይ ህይወታቸውን ላጡት መዘክር " ከተዘጋጀው መጽሔት ነው ፡፡
እየሩሳሌም በተዋሃደችበት ቀን ሃር ሄርጽል ከሚባለው ቦታ ፤የእስራኤል ፕሬዚዳንት፤ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፤ የእስራኤል ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት እንዲሁም የተለያዩ የውጣቶች ማህበርና ሰፊው የእስራኤል ዜጎች በሙታን መዘክሩ ቀን ከቦታው ይገኛሉ ፡፡
የኢትዮጵያ በህልና ቀርስ ማዕከል ዋና ሥራ አስካሃጅ በሱዳን እስራኤል ለመግባት በልጅነቱ ስላሳለፈው ችግር እንዲህ ሲል ጽፏል ፤ "
" በየቀኑ የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል ፤ ሞቱ ሽማግሌወችን ፤ ታዳጊ ህጻኖችን ፤ እሴቶችን ወንዶችን አይምርም፤ ሞት ስደተኞች በሚኖሩበት ሰፈር የዘወትር ተግባር ሆነ ፡፡ በስደተኞች ሰፈር የመታከሚያ ቦታ የለዉም ፡፡ ከስደተኞች ስፈር ራቅ ብሎ ከሚገኘው ህክምና ጣቢያ የሄደ ሰው በህይወቱ አይመለስልም ፡፡ የስደተኞች ሰፈር የሰወች መሞቻ ወጥመድ ሆነ ፡፡ ሞቱ ሌልትም ቀንም በየ ደቂቃወች ነው ፡፡ ብዙ ቤተ ሰቦች ወንዶች እሴቶች ወጣት ልጆች አዛውንትም ሁሉም እየሩሳሌም ለመግባት ፈለገው፤ ከናታቸው ማህጸን የወጡ ህጻናት በጣረ ሞት ሲሰቃዩ በመጨረሻም ህይወታቸው ስታልፍ፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩት እንደ አበባ ሲረግፉ፤
ቤተ ሰብ እንዳልነበረ ሆኖ ሲያልቅ ፤ ልጆች ያለ እናትና አባት መቅረት ፤ ወላጆቻቸውን መቅበር፤ ወንዶች ያለ ምሽት እሴቶ ያለ በዓል ፤ ወላጆች ልጆቻቸውን መቅበር ሆነ ፡፡ የሱዳን በረሃ አንድም ሰው ሳያስቀር እኛን ለማጥፋት አፉን ከፍቶ ይጠባበቃል ፡፡ ለሚሞቱትም በቂ የመቀበሪያ ቦታ የለም ፡፡ በፍርሃት ከዛፍ ሥር ተጠግተን ሰው እንዳያየነ ማንነታችን እንዳያውቁብን ቀስ እያልነ ፡፡ በዚህ የተረገመ የሱዳን አገር በበዙ ሽህ የሚቆጠሩት ሰወች የህይወት ምስዋዕት ከፈሉ " ፡፡
እንደሚታወቅው የሱዳን ጉዞ ብዙ የህይወት ምስዋዕት የተከፈለበት ነው ፡፡ እስከ አሁን የሚታወቅው ቁጥራቸው 1620 ስለሆነ ስማችው በዝርዝር ከመዘከሩ ሃውልት ተጽፎ ይገኛል ፡፡ ይሁን እንጅ ገና
ያልተመዘገቡ ሰወች ይኖሩ ይሆናል ፡፡ ( 4000 ሰወች ሙተዋል የሚሉም አሉ ) ገና አልተርጋገጠም ፡፡የቀሩትም ከሙታን መዘከሪያ ቦታ ስማቸው እንዲጻፍ ፤ የእትዮጵያ ባህልና ቅርስ መዕክል ጥረት በማድረግ ላይ ነው ፡፡
ወደ ሱዳን ሲሄዱና ሱዳን ሳሉ የሞቱትን ወገኖች ለመዘከር ጥቅምት/ 2015 ዓ/ም ከተዘጋጀው እንደ መረጃነት የተወሰደ
የሟች ስም ዝርዝር ለመሰብሰብ ሥራው በተካሄደበት ጊዜ መረዳት የተቻለው ምን ያክል ለብ ሠባሪ የሆነ
ከባድ ጥፋት ለቤተ ሰቦች ብቻ ሳይሆን ለመላው እስራኤል መድረሱን ነው ፡፡ በተካሄድው የሙታን ስም ዝርዝር ምዝገባ ሥራ ቁጥራቸው 1620 እሴቶች ወንዶችና ታዳጊ ልጆች እስራኤል አገር ለመግባት ሲሞክሩ ህይወታቸውን ያጡ መሆኑን ማራጋገጥ ተችሏል ፡፡