ስለ- የኢትዮጵያ አይሁዲ ቅርስ ማዕከል
על המרכז. איור: עלמו אישטה

ስለ ቅርሱ ማዕከል

የኢትዮጵያ ይሁዲወች ባህልና ቅርስ ማዕከል የተቋቋመው፤ የእስራኤል መንግሥት ባጸደቀው ሕግ መሰረት ሲሆን ፤ እስራኤል የገቡት ቤተ እስራኤሎች ባህል፤ ወግ ፤ ለምድና ቅርሶች
የሚጠናበትና ተከብሮ የሚቀመጥበት ማዕከል እንዲሆን በማሰብ ነው፡፡ ተቋሙ ለተለያዩ ድርጅቶች፤ ተቋማትና ለማንኛውም አካል ባካባቢና በሃገር አቀፍ ደረጃ በተቀራረበ ሁኔታ በጋራ የሚሠራና አገግሎት የሚስጥ ማዕከላዊ የሆነ ማዕከል ነው፡፡ ይህ ተቋም የምርምርና ጥናት ፤ ቤተ መዘክር ሆኖ ስለ እትዮጵያ ይሁዲወች ባህል ቅርስና ታሪክ ትምህርት ይሰጥበታል፡፡
የኢትዮጵያ ይሁዲወችታሪክ ቅርስና ባህል ማዕከል የተሻሻለና ዘመናዊ የሆነ ሲሆን ፤ በቃል የሚተረከውን ከጽሁፍ ጋር በማዛመድ የህብረተ ሰቡ ጥንታዊ የሆኑ አስደናቂ ባህልና ትርክቶች በእሥራኢል ዘመናዊ ቴክኖሎጅ አማካኝነት ፤ በመላው እስራኤል ለማስተዋወቅና ለማዳረስ ነው ፡፡ ለእስራኤል ባህል ተጨማሪ ትልቅ ሃብት በመሆን የዳበረና ሁለገብ የሆነ ማዕከል መመሥረት ሲሆን ፤ የተቋሙ ቋሚ ቦታ እየሩሳለም እንዲሆን ነው የተወሰነ ፡፡ እየሩሳለም ቤተ እስራኤሎች ከትዉልድ እስከ ትውልድ ሲመኟት የቆየች ከተማ በመሆኗ፡፡

ያባህልና የቅርስ ማዕከል ሕጋዊ ምሥረታ 2012

ፎቶግራፉን ያነሳ: ዮሲ ኮሬን

ፈንታሁን አሰፋ ዳዊት

የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባሕልና ቅርስ ማዕከል የቦርድ ሊቀ መንበር

ፈንታሁን አስፋ ዳዊት ጎንደር ከተማ አጠገብ ከሚገኘው ወለቃ ከሚባለው የቤተ እሥራኤሎች መንደር ተዎለደ፡ አንድ ቀን እየሩሳሌም እገባለሁ ብሎ ይመኝ ስለነበረ ከልጅነቱ ጀምሮ እብራይስጥ ቋንቋ እየተማረ ጸሎቱን ቀጠለ ፡፡ በ 1985 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋል በአጎቶቹና ካናዳ በሚገኘው JIAS በሚባለው የይሁዲዎች ማህበር ረዳትነት ወደ ካናዳ ሄዶ በሞንትሪያል ከተማ መኖር ጀመረ ፡፡ ከዚያም ወደ ኩቤክ ካናዳ ለሚመጡ አዲስ ገቢዎች የሚሰጠውን የሰባት ወር የፈረንሳይኛ ቋንቋ ካጠናቀቀ በኋላ ፤ ካናዳ በሚገኘው የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባቋቋሙት ድርጅት ሊቀ መንበር ሆኖ በማገልገል ላይ እያለ ኮንኮርዲያ ከሚባለው ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና (ኢንጅነሪንግ) ትምህርቱን ጀመረ ፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሆኖ ሳለ ወደ እሥራኤል ለመምጣት ወሰነ፤ በ1994 ዓ/ም እሥራኤል መጥቶ ሃይፋ ከተማ ከሚገኘው ቴክኒዮን ዩኒቨርሲቲ ገብቶ የኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ ትምህርቱን አጠናቀቀ ፡፡ ፈንታሁን ለተወሰኑ አመታት በምህንድስና ሙያው ተሰማርቶ ከሰራ በኋላ በማህበራዊና በህብረተ ሰብ ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት ለበርካታ ዓመታት በመሥራት ላይ ይገኛል ፤ ቁጥራቸው ከሽህ በላይ የሆኑ አዲስ ገቢዎችን የሚያስተነግዱ ሁለት የሶክኑት ሃየሁዲት መርካዝ ክሊጣዎች አስተዳዳሪ ሆኖም ሠርቷል ፡፡ በሲድኒ አውስትራሊያ የኬሬን ሃይሶድ ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ በዓለም ላይ በችግር ያሉንትን ይሁዲዎች ወደ እሥራኤል አምጥቶ ለማስተናገድ የሚረዳ ገንዘብ መዋጮ ለሚጠይቀው ድርጅት በሃላፊነት ከመስራቱም ባሻገር እስራኤልን በመወከል ስለ አገሪቱ ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ ገለጻ በመስጠት ሠርቷል ፡፡ ጠበቃ የሚባለው የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ህጋዊ መብትና እኩልነት ጉዳይ ተከራካሪ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ለ 7 ዓመታት ያክል ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ባገለገለበት ወቅት ዘረኛነትና አድልዎ እንዲጠፋ በሕግ አንጻር በዙ ትግሎችን አደርጓል ፤ ህጉን መሠረት በማድረግ ሁሉም ዜጋ እኩልነት እንዲኖረው ከመንግሥትና ከፖሊስ ሠራዊት ጋር በመነጋገርና በመደራደር ፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ ይሁዲዎች በኩል የህብረተ ሰብ ሃላፊዎችና አስተዳዳሪ የሚሆኑ ወጣቶችን በማሰልጠን ዘርፎች ሠርቷል ፡፡ ፈንታሁን የትዳር አጋሩ ከሆነችው ከ/ሮ ኤፍራት አምስት ልጆች አሉት፤ ከቴክኒዮን ዩኒቨርሲቲ BSc የኤሌክትሪክ ኢንጅነሪንግ ዲግሪ ባለቤት ነው ፡፡ እብራይስጥ ፤እንግሊዝኛ ፤አማርኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን ይናገራል ፡፡

ምክር ቤት / ኮሚቴ

ሞሼ ባሩኽ

የ”ቤተ እስራኤል” የሽቫ መሪ
የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ጥናት ተቋም ኃላፊ
ማህበረሰባዊ የሀይማኖት ራብ በአሽዶድ ከተማ

ራሄሊ ካፕላን

በአኑ የይሁዳውያን ቤተ መዘክር የስልታዊና የሽርክ ግንኙነት ሃላፊ

ቲራ ጋሊኖይር

በትምህርት ሚኒስቴር የአዲስ ገቢ ይሁዳውያን ልጆች አስተባባሪ ክፍል ሃላፊ

ማታን ስጦታው ማለደ

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የባጀት ክፍል ሠራተኛ

ምናኼም ሰንበቱ

የሕግ ጠበቃ/ ባለሙያ

ፕሮፌሶር ራኼል ሻርዓቢ

የአሽኬሎን ከተማ ኮሌጅ የሶሲዮሎጅ ክፍል ዋና ሃላፊ

አዳም ተሰማ

በአልያና ክሊታ ጽህፈት ቤት የእሥራኤል ብሄራዊ ቅርሶች ፤ ድርጅቶች ፤ ተቋማትና ህብረተ ሰብ ክፍል ሃላፊ

ፍሮፌሶር ሊአ ማኮቭጽኪ

የታሪክ ፕሮፌሶርና በአሬኤል ዩኒቨርሲቲ የእሥራኤል ዘመናዊ ታሪክ ጥናትና ምርምር ክፍል ሃላፊ

አሳፍ ታርከቲንስኪ

በእሥራኤል ብሔራዊ ቤተ መዘክር የምርምርና የማስፋፋት ክፍል ሃላፊ

የሳይንስ ጉዳይ ኮሚቴ

Photo: Revital Topiol

ዶ/ር ሲምኻ ጌታሁን

የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባሕልና ቅርስ ማዕከል የቦርድ ሊቀ መንበር የነበሩት

የኢትዮጲያ ይሁዳውያን ባህልና ቅርስ ማዕከል፤ ጥልቅ የሆነ ጥናት የተደረገበትና የሚደርግበት ማዕከል ሆኖ ፤ የቤተ እሥራኤሎች አስደናቂ ታሪክ ካጠቃላይ የይሁዲዎች ታሪክ ባላነሰ ደረጃ የሚታይ ሆኖ ለሰፊው ህብረተ ሰብ ተደራሽ ለማድረግ ነው ፡፡ የማዕከሉ አይነተኛ ዓላማ ፤ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ታሪክ ካጠቃላይ እሥራኤላዊ ይሁዲዎች ታሪክ ጋር በተመሳሳይ ደረጃ በክብር ቦታ የሁሉም ታሪክ እንዲሆን ፤ በተለይ ለህብረተ ሰባችን አዲስ ትውልድ ፡፡
የባህልና ቅርስ ማዕከሉ በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙት የእሥራኤል ህብረት ሰብና ፤ ለኢትዮጲያ ይሁዲዎች ፤ በራፉን ክፍት አድርጎ ይጠብቃል ፡፡ የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት ሰዎችም ፤ አስደማሚ የሆኑ የተቀረጹ መረጃዎችን ፤ ሠነዶችን ፤ የምስክር ወረቀቶችን እና ደብዳቢዎችን በማየት ቤተ እሥራኤሎች ኢትዮጵያ እንዴት ብለው እንደኖሩ መረጃዎችን የገኛሉ ፡፡ ወጣቱ ትውልድ በበኩሉ እስከ ዛሬ ያላወቃችውን አኩሪ የሆኑ መረጃዎችና አስደናቂ ታሪክ ሊያገኝ ይችላል ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ፤ ቤተ እሥራኤሎች ከሌሎች ይሁዲዎች ርቀው ለብዙ ዓመታት በችግር እያሉ ባህልና ቅርሶችን ጠበቀው ስለመኖራችው ፤ የኢትዮጵያ ባህልና ቅርስ ማዕከል ማስረጃዎችን ይፋ በማድረግ ሁሉም እንዲገለገሉበት ያደርጋል ፡፡
የቤተ እሥራኤሎች ታሪክ ልዩና እጅግ አስደናቂ ነው ፤ በመላው ዓለም ተሰደው ከሚኖሩት ይሁዲዎች ተለይተውና ርቀው ለብዙ ሽህ ዓመታት ተቸግረውና ተጨቆነው ሲኖሩ ተስፋ ባለመቁረጥ የይሁዲ ሃይማኖታቸውን ለመጠበቅም ከባድ ምስዋዕቶችን መክፈላቸው ፤ ለመላው ይሁዲ ቀጣይነትና አንድነት መሰረታዊና አኩሪ የሆነ የመንፈሳዊ ምሳሌዎች ሆነዋል ፡፡
የኢትዮጲያ ይሁዲዎች ጥንካሬ ምን የህል እንደሆነ ማወቅ የሚቻለው ውጣቱ ትውልድ ቀደም የነበረውን የአባቶች ባህል ፤ ልምድና ታሪክ መሰረት አድርጎ እንደገና እየፈተሽና እየተመራመረ መሆኑ ነው ፡፡
የታዋቂዎች የጊድዖን ነገሥታት ዘር የሆንኩትና የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ባህልና ቅርስ ማዕከል መሥራችና ሊቀ መንበር ፤ ታሪኬን ፤ ባህሌን ፤ አመጋገቤን ፤ ቋንቋየን ነው ተምሬ ያደኩት ፤ ዋና ዓላማየና ፍላጎቴም ፤ ባህላዊና ትምህርታዊ ፍሬ ነገሮች ሁሉ ፍላጎት ቀስቃሽና አነቃቂዎች ሆነው አሁን ላለውና ለቀጣዩ የእሥራኤል ህበርተ ሰብ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው ፡፡
የዚህ ተቋም መሥራችና ሊቀ መንበር በመሆኔ ትልቅ ኩራትና ክብር ይሰማኛል ፤ እኔም ተቋሙ አሁን ላለውና ለተተኪው ትውልድ ጠቃሚ እንዲሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ተግቸና ጠንክሬ አሠራለሁ ፡፡

ፕሮፈሶር ባት ጺዮን ዓራቂ ክሎርማን

በኦፕን ዩኒቨርሲቲ ፤ የታሪክ የፊሎሶፊና የይሁዳውያን ታሪክ ምርምር ክፍል ፕሮፌሰር

ፕሮፌሶር ጋሊያ ጻባር

ፕሮፌሶር ኻጋይ ኤርሊኽ

በቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪቃና የመካከለኛው ምሥራቅ ታሪክ ትሮፌሶር ( ጡረታ የወጡ)

ዶ/ር አንበሴ ተፈራ

የምርምርና ጥናት ቡድን ሊቀ መንበር

የባህልና ቅርስ ተቋሙ ሠራተኞች

ቪኪ ሄንደልማን

የማዕከሉ ኒው መዲያ ክፍል ሃላፊ

ጋዲ ጌታ መላኩ

ማስረጃዎችን የማሰባሰብ ክፍል ሃላፊ

ዮሲ መንግሥቱ

የማዕከሉ የፕሮጀክቶች ክፍል ሃላፊ

ታማር ጋርደን

የማዕከሉ የምርምር ክፍል ረዳት

ሣራ ገዳሙ

የማዕከሉ ጽህፈት ቤት የሥራ ሃላፊ