የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባሕልና ቀርስ ማዕከል ፤ የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ታሪክ የሚገልጹ መረጃዎችን አሰባስቦ እየመዘገበ በማስቀመጥ ተጠቃሚዎች እንዲገለገሉባቸው ዕድሎችን አመቻችቷል ፡፡ ከመዝገብ ቤቱ፤ የተለያዩ ሠነዶች ፤ፎቶ ግራፎች ፤ቪዲዮ ክሊፖች ፤ በድምጽ የተቀረጹ መረጃዎች ፤ጋዜጦች ፤ የዕደ ጥበብ ሥራ ወጤቶች በትርዒት፤ ልዩና ድንቅ የሆኑት የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ባሕልና ቅርሶች ፤ ይሁዲነታችው ዕውቅና እንዲያገኝ ስላደረጉት ትግል፤ ወደ እሥራኤል አመጣጥና በእሥራኤል አኗኗር የሚገልጹ መረጃዎች በመዝገብ ቤቱ ይገኛሉ ፡፡
በመዝገብ ቤቱ ከተቀመጡት መረጃዎች በተጨማሪ ፤ የኢትዮጵያ ይሁዲ ታሪካዊ ቅርሶች በቃል ከትውልድ እስከ ትውልድ ሲተላለፉ የቆዩ መሆናችው ይታወቃል ፡፡ እነዚህ ቅርሶች ለቀጣዩ ትውልድ እንዲሻገሩ ታሳቢ በማድረግ ፤ የመንፈሳዊ አባቶችን ፤ አዛውንቶችን ፤ የጺዎን እሥረኞች፤ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች እሥራኤል እንዲመጡ የታገሉት ፤ ከኢትዮጵያ እሥራኤል የገቡት የመጀመሪዎች ሰዎች ሁሉ ፤ ታሪካዊ ሥራቸው ተቀርጾና ተጽፎ ውልድ ትውልድ እንዲያውቀው ለማድረግ ፤ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ባሕልና ቅርስ ማዕከል ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሠራ ነው ፡፡
የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባሕልና ቅርስ ማዕከል ለትውልድ ጠቃሚ የሚሆኑ መረጃዎችን እየፈለገና እያፍላለገ ከማዕከሉ መዝገብ ቤት የማስቀመጥ ሥራውን እንደቀጥሏል ፡፡ ይህ ሥራችን የተሟላና ሁለገብ ሆኖ ማንኛዉም ሰው ሊጠቀምበት የሚችል መዝገብ ቤት / ቤተ መዘክር እንዲሆን ፤ የተለያዩ የመረጃ፤ ሠነዶች ፤ፎቶ ግራፎች ፤ በፊልምና በድምጽ የተቀረጹ ሠነዶችን ፤ ለታሪክ ቢቀመጡ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችና መስክር ወረቀቶችን ለኢትዮጵያ ይሁዲዎች ባሕልና ቅርስ ማዕከል በመስጠት እናንተም የዚህ ታሪካዊ ተግባር ተሳታፊዎች ትሆኑ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን ፡፡
የሚደርሱነን መረጃዎች ሁሉ ስም እየሰጠን በመዝገብ ቤቶች ሕግልና ደንብ መሠረት ፤መረጃ የማግኘት ፤ የግለ ሰብ ከብር አለመንካትና በሌላ ግለ ሰብ የተዘጋጀውን በራሱ የተዘጋጀ እድያስመስል በመጠበቅ ሥነ ሥርዓት ያለው አገልግሎት ለሰፊው ሕዝብ መስጠት ጀምረናል ፡፡
ከቤተ መዘክሩ ባሉት ሰነዶች መገለግል የሚቻል፤ የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባሕልና ቅርስ ማዕከል በድህረ ገጹ ይፋ ባደረገው መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡
አፈላጊ የሆኑ መረጃወችን ከመዝገብ ቤታችን ለማግኘትና ለዕርዳታ፤ በኢሜል አድራሻችን ጠይቁን፡፡