ፈንታሁን አሰፋ ዳዊት
የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ባሕልና ቅርስ ማዕከል የቦርድ ሊቀ መንበርምክር ቤት / ኮሚቴ
ሞሼ ባሩኽ
የ”ቤተ እስራኤል” የሽቫ መሪ
የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ጥናት ተቋም ኃላፊ
ማህበረሰባዊ የሀይማኖት ራብ በአሽዶድ ከተማ
ራሄሊ ካፕላን
በአኑ የይሁዳውያን ቤተ መዘክር የስልታዊና የሽርክ ግንኙነት ሃላፊ
ቲራ ጋሊኖይር
በትምህርት ሚኒስቴር የአዲስ ገቢ ይሁዳውያን ልጆች አስተባባሪ ክፍል ሃላፊ
ማታን ስጦታው ማለደ
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የባጀት ክፍል ሠራተኛ
ምናኼም ሰንበቱ
የሕግ ጠበቃ/ ባለሙያ
ፕሮፌሶር ራኼል ሻርዓቢ
የአሽኬሎን ከተማ ኮሌጅ የሶሲዮሎጅ ክፍል ዋና ሃላፊ
አዳም ተሰማ
በአልያና ክሊታ ጽህፈት ቤት የእሥራኤል ብሄራዊ ቅርሶች ፤ ድርጅቶች ፤ ተቋማትና ህብረተ ሰብ ክፍል ሃላፊ
ፍሮፌሶር ሊአ ማኮቭጽኪ
የታሪክ ፕሮፌሶርና በአሬኤል ዩኒቨርሲቲ የእሥራኤል ዘመናዊ ታሪክ ጥናትና ምርምር ክፍል ሃላፊ
አሳፍ ታርከቲንስኪ
የሳይንስ ጉዳይ ኮሚቴ
ዶ/ር ሲምኻ ጌታሁን
የኢትዮጲያ ይሁዳውያን ባህልና ቅርስ ማዕከል፤ ጥልቅ የሆነ ጥናት የተደረገበትና የሚደርግበት ማዕከል ሆኖ ፤ የቤተ እሥራኤሎች አስደናቂ ታሪክ ካጠቃላይ የይሁዲዎች ታሪክ ባላነሰ ደረጃ የሚታይ ሆኖ ለሰፊው ህብረተ ሰብ ተደራሽ ለማድረግ ነው ፡፡ የማዕከሉ አይነተኛ ዓላማ ፤ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ታሪክ ካጠቃላይ እሥራኤላዊ ይሁዲዎች ታሪክ ጋር በተመሳሳይ ደረጃ በክብር ቦታ የሁሉም ታሪክ እንዲሆን ፤ በተለይ ለህብረተ ሰባችን አዲስ ትውልድ ፡፡
የባህልና ቅርስ ማዕከሉ በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙት የእሥራኤል ህብረት ሰብና ፤ ለኢትዮጲያ ይሁዲዎች ፤ በራፉን ክፍት አድርጎ ይጠብቃል ፡፡ የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት ሰዎችም ፤ አስደማሚ የሆኑ የተቀረጹ መረጃዎችን ፤ ሠነዶችን ፤ የምስክር ወረቀቶችን እና ደብዳቢዎችን በማየት ቤተ እሥራኤሎች ኢትዮጵያ እንዴት ብለው እንደኖሩ መረጃዎችን የገኛሉ ፡፡ ወጣቱ ትውልድ በበኩሉ እስከ ዛሬ ያላወቃችውን አኩሪ የሆኑ መረጃዎችና አስደናቂ ታሪክ ሊያገኝ ይችላል ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ፤ ቤተ እሥራኤሎች ከሌሎች ይሁዲዎች ርቀው ለብዙ ዓመታት በችግር እያሉ ባህልና ቅርሶችን ጠበቀው ስለመኖራችው ፤ የኢትዮጵያ ባህልና ቅርስ ማዕከል ማስረጃዎችን ይፋ በማድረግ ሁሉም እንዲገለገሉበት ያደርጋል ፡፡
የቤተ እሥራኤሎች ታሪክ ልዩና እጅግ አስደናቂ ነው ፤ በመላው ዓለም ተሰደው ከሚኖሩት ይሁዲዎች ተለይተውና ርቀው ለብዙ ሽህ ዓመታት ተቸግረውና ተጨቆነው ሲኖሩ ተስፋ ባለመቁረጥ የይሁዲ ሃይማኖታቸውን ለመጠበቅም ከባድ ምስዋዕቶችን መክፈላቸው ፤ ለመላው ይሁዲ ቀጣይነትና አንድነት መሰረታዊና አኩሪ የሆነ የመንፈሳዊ ምሳሌዎች ሆነዋል ፡፡
የኢትዮጲያ ይሁዲዎች ጥንካሬ ምን የህል እንደሆነ ማወቅ የሚቻለው ውጣቱ ትውልድ ቀደም የነበረውን የአባቶች ባህል ፤ ልምድና ታሪክ መሰረት አድርጎ እንደገና እየፈተሽና እየተመራመረ መሆኑ ነው ፡፡
የታዋቂዎች የጊድዖን ነገሥታት ዘር የሆንኩትና የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ባህልና ቅርስ ማዕከል መሥራችና ሊቀ መንበር ፤ ታሪኬን ፤ ባህሌን ፤ አመጋገቤን ፤ ቋንቋየን ነው ተምሬ ያደኩት ፤ ዋና ዓላማየና ፍላጎቴም ፤ ባህላዊና ትምህርታዊ ፍሬ ነገሮች ሁሉ ፍላጎት ቀስቃሽና አነቃቂዎች ሆነው አሁን ላለውና ለቀጣዩ የእሥራኤል ህበርተ ሰብ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው ፡፡
የዚህ ተቋም መሥራችና ሊቀ መንበር በመሆኔ ትልቅ ኩራትና ክብር ይሰማኛል ፤ እኔም ተቋሙ አሁን ላለውና ለተተኪው ትውልድ ጠቃሚ እንዲሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ተግቸና ጠንክሬ አሠራለሁ ፡፡
ፕሮፈሶር ባት ጺዮን ዓራቂ ክሎርማን
በኦፕን ዩኒቨርሲቲ ፤ የታሪክ የፊሎሶፊና የይሁዳውያን ታሪክ ምርምር ክፍል ፕሮፌሰር
ፕሮፌሶር ጋሊያ ጻባር
ፕሮፌሶር ኻጋይ ኤርሊኽ
በቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪቃና የመካከለኛው ምሥራቅ ታሪክ ትሮፌሶር ( ጡረታ የወጡ)